በየካ ክ/ከተማ የደጃዝማች ወንድይራድ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሚከተሉትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በየካ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት ደጃ/ወንድይራድ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
የእቃ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
በየካ ክ/ከተማ የደጃዝማች ወንድይራድ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሚከተሉትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት አንድ ደንብ ልብሶች
- ሎት ሁለት ልዩ ልዩ አላቂ እቃዎች
- ሎት ሦስት ልዩ ልዩ አላቂ የጽዳት እቃዎች
- ሎት አራት ልዩ ልዩ የተገጣጣሚና የጥገና እቃዎች
- ሎት አምስት ልዩ ልዩ የቤት የቢሮ እቃዎች
በጨረታው ለመሣተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች በሙሉ የሚከተሉትን ከ1-10 ያሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቾች የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የቫት ተመዝጋቢና ታክስ ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ለመውሰድ ሲመጡ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ/ በመክፈል ከት/ቤቱ ግዥ ክፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ለጨረታ ማስረከቢያ ተመላሽ የሚሆን ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ CPO /ከሎት አንድ እስከ ሎት አራት ለእያንዳንዳቸው ብር 2000.00 / ሁለት ሺ /፣ ለሎት አምስት / 5000 / አምስት ሺ ብቻ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በፖስታ ውስጥ ተያይዞ በጨረታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የምትጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተመለከት መሰረት ከነቫቱ በማሰብ ጠቅላላ ዋጋ ላይ በታሸገ ፖስታ ማህተም ባረፈበት ኦርጂናልና ኮፒ እሽግ ለይቶ በማዘጋጀት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ውጤት እንደታወቀ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ የሚውለው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ድረስ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በማግስቱ /በአስራ አንደኛው/ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ታሽጎ ፣ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 5 ጨረታው ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉትን ዕቃ በራሳቸው ትራንስፖርት አጓጉዘው ት/ቤቱ ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ አለባቸው::
- ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሰው ማቅረብ አይችሉም፡፡
- ተጫራቶች ከጨረታ መክፈቻ ቀን በፊት ባሉት ቀናት ውስጥ ለሚወዳደሩበት እቃ በየአይነቱ ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው::
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻችን ፡- ኮተቤ ደጃዝማች ወንድይራድ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በስተጀርባ በኩል 300 ሜትር
ገባ ብሎ ሲሆን ለበለጠ መረጃ ደጃ/ወንድይራድ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ስልክ ቁጥር 011 645 61 99
በየካ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት ደጃ/ወንድይራድ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
