የደቡብ ኢትዮጵያ /ክ/መ/ጤና ቢሮ ለ11ወራት ለመስክ ሥራ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ሀርድ ቶፕ ማርክ 2 ሞዴል 2024 ወይም 2025 የሆነ የመኪና ኪራይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ብቃት ካላቸው ድርጅቶች አገልግሎቱን ለመከራየት ይፈልጋል።
South Ethiopia Regional Health Bureau (የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ኢትዮጵያ /ክ/መ/ጤና ቢሮ ለ11ወራት ለመስክ ሥራ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ሀርድ ቶፕ ማርክ 2 ሞዴል 2024 ወይም 2025 የሆነ የመኪና ኪራይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ብቃት ካላቸው ድርጅቶች አገልግሎቱን ለመከራየት ስለሚፈልግ መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች :-
- በመስኩ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የአቅራቢ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ወይም ሰርቲፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ፣
- ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ዶክመንት የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ቀናት በቢሮ የግዥ ፋይናንስ ንብ/አስ/ ዳይሬክተር በመቅረብ መግዛት ይችላሉ ።
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና 30,000.00 /ሰለሳ ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ወይም ባንክ ዋስትና ከቴክኒካል ኦርጂናል ሠነድ ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
- ከዚህ በፊት በመስኩ አገልግሎት የሰጡበት የመልካም ሥራ አፈፃፀም የምስክር ወረቀት ከመንግሥታዊ መ/ቤት ወይም ተቋማትና ከሌሎች ህጋዊ ዕውቅና ካላቸው ድርጅቶች ቢያንስ ለ 1 ዓመት አገልግሎት የሰጡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንት ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ እያንዳንዳቸው ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ እና ጠቅላላ በአንድ ሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:00-6:00 ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ መክተት አለባቸው።
- ጨረታ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8:30 ሰዓት ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
- የሚሳተፉ ድርጅቶች ለሚያቀርቡት የመኪና ኪራይ ጥራቱን የጠበቀ እና በተጠየቀው መጠይቅ መሠረት እንዲያቀርቡ ይጠየቃል፡፡
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ጤና ቢሮ
ጂንካ
