የወልቂጤ ዕጽዋት ዘር ጥራት ቁጥጥር ምርመራ ማዕከል ለስራ አገልግሎት የሚውል Dry oven for plant seed Laboratory በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የወልቂጤ ዕጽዋት ዘር ጥራት ቁጥጥርና ምርመራ ማዕከል
የእቃ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የወልቂጤ ዕጽዋት ዘር ጥራት ቁጥጥር ምርመራ ማዕከል ለስራ አገልግሎት የሚውል Dry oven for plant seed Laboratory በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፤፤
- ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያሳይ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው በአቅራቢዎች ስም ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ
- ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፤ እንዲሁም /TIN NUMBER/ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በወልቂጤ ዕጽዋት ዘር ጥራት ቁጥጥር ቢሮ ቁጥር 3 ህጋዊ ፍቃዳቸውን በመያዝ በማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ CPO ከጠቅላላ ዋጋ 2% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ በ15 ቀናት ውስጥ የወልቂጤ ዕጽዋት ዘር ጥራት ቁጥጥር ምርመራ ማዕከል ቢሮ ቁጥር 3 ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፤
- አንድ ተጫራች ሌላው ባቀረበው ዋጋ ተንተርሶ የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፤
- ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ አልያም የህዝብ በአል ከሆነ የመክፈቻ ቀን በቀጣይ ባለ የስራ ቀን ይሆናል፤
ማሳሰቢያ ፡- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ፡- ከዚህ በታች በተጠቀሱት ስልክ ቁጥሮች ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡ 0113301349 0912158786፤ 0935702167፤ 0911776041
የወልቂጤ ዕጽዋት ዘር ጥራት ቁጥጥርና
ምርመራ ማዕከል
