Tender Detail

Tender Details

  • Company የጎተራ ማሳለጫ ጤና ጣቢያ
  • Address ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል ፍላወር 300 ሜትር ገባ ብሎ በስተ ግራ በኩል ያሬድ ቤተ ክርስቲያ ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 470 0844
  • Website
  • Deadline01 Mar 2025, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Pharmaceutical Products

የጎተራ ማሳለጫ ጤና ጣቢያ በ2017 በጀት 2ኛ ዙር ለመ/ቤታችን አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የጎተራ ማሳለጫ ጤና ጣቢያ


 

የጨረታ ማስታውቂያ

 

የጎተራ ማሳለጫ ጤና ጣቢያ በ2017 በጀት 2ኛ ዙር ለመ/ቤታችን አገልግሎት የሚውል

      ሎት 1. አላቂ የቢሮ ዕቃ

      ሎት 2. የጽዳት ዕቃዎች

      ሎት 3. ደንብ ልብስ

      ሎት 4. መድሃኒቶች

      ሎት 5. ሪኤጀንቶችን

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ተጫራቾች ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን /2016 /ግብር ከፍለው ፈቃዳቸውን ያደሱ፣ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋዮች መሆናቸውን የሚገልጽና ከአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
  • በጨረታው ለማሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከመ/ቤቱ ረዳት ፋይናንስ ኦፊሰር ማግኘት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች ለሚጫረቱት ሎት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ CPO ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ለሎት 1 ብር 2,000.00፣ ሎት 2. 3,000.00፣ ሎት 3. 3,000.00፣ ሎት 4. 5,000.00፣ ሎት 5. 5,000.00
  • ተጫራቾች የሚጫረቱት የጨረታ ሰነድ ሞልተው ኦርጅናል ሰነድ ላይ ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነድ ላይ ኮፒ በማለት ለየብቻቸው በማሸግ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ከተው በሁለቱም ዶክመንት ላይ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ በመንግስት የስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዕቃ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ሆኖም ግን ናሙና የሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ ይገለጻል።
  • በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም በሌሉበት ይከፈታል።
  • ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ ጎተራ ማሳለጫ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ነው።
  • የጨረታው አሸናፊ የአሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት ጤና ጣቢያው ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
  • ግዥ ፈጻሚው መ/ቤት ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ከተገለጸው የግዥ መጠን ላይ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • አድራሻችን፡- ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል ፍላወር 300 ሜትር ገባ ብሎ በስተ ግራ በኩል ያሬድ ቤተ ክርስቲያ ፊት ለፊት
  • ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር 011 470 0844 መጠየቅ ይችላሉ።

 

የጎተራ ማሳለጫ ጤና ጣቢያ

 

Save Tender