የደሴ ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ እና የደሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የ2017 በጀት አመት የዘመኑን የካዳስተር ስራ ለማሰራት እና የኤሌክትሮኒክስ የማዘጋጃዊ አገልግሎት ማዘመኛ ለሶፍትዌር ለስራው አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የደሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የደሴ ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ እና የደሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የ2017 በጀት አመት የዘመኑን የካዳስተር ስራ ለማሰራት እና የኤሌክትሮኒክስ የማዘጋጃዊ አገልግሎት ማዘመኛ ለሶፍትዌር ለስራው አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ እቃዎች
ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ፣
ሎት 2 ቋሚ እቃዎች፣
ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልፅ ጨረታ በማወዳደር አሸናፊውን በመለየት በኮንትራት ውል ይዞ መግዛት ይፈልጋል
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል።
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላችሁ፣
- ግዥው ከ200,000 ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት ተመዝጋቢ የሆነና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ሲመጡ ከላይ ከ እስከ 3 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በነፃ ከግዥ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 18 ሶስተኛ ፎቅ ከ12/6/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 26/6/2017 ዓ.ም 11፡30 ድረስ ደሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በግዥ ፋይናንስ ቡድን ሶስተኛ ፎቅ ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝና ፍሉድ መደረግ የለበትም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ድምር 2% ከባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው እንዲሁም አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ያሸነፈበትን ዋጋ 10% የውለታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በመሙላት በፖስታ በማሸግ ደሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 18 3ኛ ፎቅ ላይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 27/06/2017 ዓ.ም 3፡30 ሰዓት ድረስ ሰነዱን በማስገባት ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ27/06/2017 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ላይ ደሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በግዥ ቢሮ ቁጥር 18 ሶስተኛ ፎቅ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይሆናል፡፡
- ውድድሩ የሚካሄደው በሎት ድምር ዋጋ ወይም በጥቅል ድምር ውጤት ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
- ስለጨረታው ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስ.ቁ 033 312 0617 ደውለው መረዳት ይችላሉ፡፡
የደሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ
