በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በሻሻመኔ ከተማ መስተዳድር የሻሸመኔ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የውሃ ቆጣሪዎች፤ የሰራተኛ የደንብ ልብሶች እና አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የሻሸመኔ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በሻሻመኔ ከተማ መስተዳድር የሻሸመኔ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
- የውሃ ቆጣሪዎች፡
- የሰራተኛ የደንብ ልብሶች
- አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎች
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋበዛሉ።
- ዕቃዎቹን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ 1% ሲፒኦ ወይም ቢድ ቦንድ ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከሻሸመኔ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ አስተዳደርና ሎጀስቲክ ከፍል በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን (ቴክኒከና ፋይናንሽል ለየብቻ) በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ (ፖስታ) ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 6፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡበት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ጋር መሆኑን ወይም አለመሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የዕቃውን ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ተመላሽ የሚሆነው አሽናፊው ድርጅት በጽሁፍ ከተገለፀ በኋላ ይሆናል።
- የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተሰጠው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በጽሑፍ እንደተገለጸ አስፈላጊውን የጨረታ ውል ማስከበሪያ ገንዘብ በማስያዝ በሻሸመኔ ከተማ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ውል መፈራረም አለበት። ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።
- የእቃዎች ርክክብ የሚካሄደው በሻሻመኔ ከተማ ውኃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግምጃ ቤት ይሆናል።
- የእቃው ብዛት (Quantity) የሚወሰነው በመስሪያ ቤቱ (በድርጅቱ) የበጀት ሁኔታ ላይ ተመርኩዞ ነው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጮች ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ሆኖ ከበጀታችን በላይ የሚሆነውን መቀነስ ወይም መጨመር የምንችል መሆኑን እንገልጻለን።
አድራሻ ስልከ ቁጥር 09 16 871 624/ 09 16 581 638/ 09 16 002 432
የሻሸመኔ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
