የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን ከገንዘብ ሚኒስቴር የመንግስት የልማት ድርጅቶች ባለአደራ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል የተላለፉለት በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ግቢ የሚገኙ በመለዋወጫ መልክ የሚሸጡ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በመለዋወጫ መልክ የሚሸጡ ተሽከርካሪዎች
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር LAMC/BD/03-06/2017
የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን ከገንዘብ ሚኒስቴር የመንግስት የልማት ድርጅቶች ባለአደራ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል የተላለፉለት በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ግቢ የሚገኙ በመለዋወጫ መልክ የሚሸጡ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መመዘኛዎች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ግሎባል በሚገኘው ከንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ጀርባ ባለው የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት ፋይናንስ ክፍል በመምጣት የንብረቶችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣
- ንብረቶቹ የሚገኙበት አድራሻ ሳሪስ አቦ አካባቢ በሚገኘው በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ ነው::
- ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በመለዋወጫ መልክ የሚሸጡ ተሽከርካሪዎች በተራ ቁጥር 2 ላይ በተጠቀሰው ቦታ /አድራሻ/ በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረቶች የጨረታ መነሻ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት ፋይናንስ ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የካቲት 27 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ በ5፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ይደረጋል፣
- የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒአ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፣
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልከ ቁጥር 0910-12-29-08/ 0912-13-47-91 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣
- ኮርፖሬሽኑ በማናቸውም ጊዜ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን
