በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር 93ኛ እግረኛ ክፍለ ጦር አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን ባለው በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር 93ኛ እግረኛ ክፍለ ጦር
የጨረታ ማስታወቂያ
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር 93ኛ እግረኛ ክፍለ ጦር አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን ባለው በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1፡- የፅሕፈት ዕቃዎች
ሎት 2፡- የትምህርት መርጃ ዕቃዎች
ሎት 3፡- የፅዳት ዕቃዎች
ሎት 4:- የቀላል ተሸከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች
ሎት 5፡- የግንባታ ጥገና አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም ለተጨማሪ እሴት ታክስ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከናወነው በግልፅ ጨረታ ስነ-ስርዓት እና ይሄንኑ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ባወጣው የመንግስት ግዥ አዋጅ መሰረት ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች ነው።
- ፍላጎት ያላቸው ብቁ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ሊያገኙ የሚችሉት መከላከያ 93ኛ እግረኛ ክፍለ ጦርግዥ ቢሮ ሲሆን የጨረታ ሰነዶች የሚመረመሩት ከዚህ በታች በቁጥር 7 (ሀ) በተገለፀው አድራሻ ነው።
- የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር = 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል በአማረኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከዚህ በታች በቁጥር 7 (ሀ) በተገለፀው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በቁጥር 7 (ሐ) በተገለፀው አድራሻ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት እና ሰነዱን ከገዛችሁበት ጊዜ አንስቶ ሳጥኑ እስከሚከፈትበት ጊዜ ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ከታወቀ ባንክ ሲ.ፒ.ኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ ብር ለሎት 1፡- 6,000 ብር፣ ለሎት 2፡- 4,000 ብር፣ ለሎት 3:-28,874 ብር ፤ ለሎት 4:- 40,000 ብር፣ ለሎት 5:- 10,000 ብር ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጨረታው የተጫራቾች ወይም የተጫራች ወኪሎች በተገኙበት በቁጥር 7 (መ) በተገለፀው አድራሻ የካቲት 26/06/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ታሽጎ 5፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የመከላከያ 93ኛ እግረኛ ክፍለ ጦር እንደ አስፈላጊነቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለማብራሪያና ጨረታ ሰነድ ማስገቢያ-
ሀ. ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄ :- መከላከያ 93ኛ እግረኛ ክፍለ ጦር ግዥ ክፍል ስልከ ቁጥር 0114-709571
ለ. ሰነዱ ወጪ የሚሆንበት አድራሻ :- 7 (ሀ) ይመልከቱ
ሐ. ጨረታው የሚላክበት አድራሻ፡- ሳሪስ አዋሽ ቆዳ ፋብሪካ አጠገብ መከላከያ 93ኛ እግረኛ ክፍለ ጦር ቅጥር ግቢ ግዥ ቢሮ
መ. ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ ፡- 7 (ሐ) ይመልከቱ ወይም የከ/ጦሩ የመሰብሰቢያ አዳራሽ
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር 93ኛ እግረኛ ክፍለ ጦር
