Tender Detail

Tender Details

  • Company Gosh Meda Pipe & Plastic Manufacturing Enterprise (የጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት)
  • Address ደሴ ከተማ ፡ ደሴ/ ገራዶ አግሮስቶን ቅጥር ግቢ ውስጥ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-62-99-99-33
  • Website
  • Deadline10 Mar 2025, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting System Design

የጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት የሂሳብ አሰራሩን በIFRS መሠረት ለመተግበር ከIFRS አማካሪ ድርጅት የማማከር አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል፡፡

Gosh Meda Pipe & Plastic Manufacturing Enterprise (የጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት)


 

የIFRS የማማከር አገልግሎት ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር GMPPME/03/2017/Local

 

የጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት የሂሳብ አሰራሩን በIFRS መሠረት ለመተግበር ከIFRS አማካሪ ድርጅት የማማከር አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል፡፡ የIFRS የማማከር አገልግሎት ስራው በፋብሪካው አድራሻ በደሴ ከተማ ገራዶ አግሮስቶን ቅጥር ግቢ የሚከናወን መሆኑን እየገለጽን ለአገልግሎት ግዥው ይህን ግልጽ ጨረታ ያወጣን ሲሆን በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ አማካሪ ድርጅቶች የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. በሙያው ለ2017 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ ከAbbey የተሰጠና የታደሰ የአማካሪነት የሙያ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት (TIN Certificate) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ (VAT) ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በፋብሪካው የፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
  3. ለጨረታ ማስከበሪያ የተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT) ጨምሮ የጠቅላላ የአገልግሎት ዋጋውን 2% ከባንክ በተዘጋጀ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ አለበት፡፡
  4. ተጫራቾች ከላይ በተ.ቁ.1 ላይ የተገለፁትን የሕጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶችን ኮፒና የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን በፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 6 ለዚሁ ጉዳይ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ22ኛው ቀን ቢሮ ቁጥር 6 ከቀኑ 8፡15 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 22ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ የሕዝብ በዓል ቀን ከሆነ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
  6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  7. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ድርጅቱ ድረስ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 09-62-99-99-33 / 09-20-78-15-79 /09-91-84-19-10 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

የጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ

 

Save Tender