የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የግዥ አፈጻጸም ሥርዓትን ለመወሰን ባወጣው መመሪያ ቁጥር 05/2011 መሰረት ከታች የተገለጸውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
Public Servants Social Security Administration (የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር)
የጨረታ ማስታወቂያ
የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የግዥ አፈጻጸም ሥርዓትን ለመወሰን ባወጣው መመሪያ ቁጥር 05/2011 መሰረት ከታች የተገለጸውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 የሲኒማ አዳራሽ ሳውንድ ሲስተም
- ሎት 2 የመሰብሰቢያ አዳራሽ ሳውንድ ሲስተም
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ማስረጃ (ክሊራንስ) ከገቢዎች ሚኒስቴር የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ በየሎቱ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከአራት ኪሎ ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ህጻናት እና ወጣቶች ቴአትር ፊት ለፊት የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ከግዥ ዳይሬከቶሬት ቢሮ መግዛት የሚችሉ ሲሆን የሚጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት የቴክኒካል እና የፋይናንሽያል ሰነድ በኮፒ እና ኦርጅናል ለየብቻ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለተፈላጊ አቅርቦቶች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት የብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው::
- ጨረታው አየር ላይ በዋለበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈተውም በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቻው በተገኙበት ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ነው:: 16ኛው ቀን የእረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው ከላይ በተገለጸው ሰዓት በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- አስተዳደሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር ፡- 011-1-23-26-96
የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር
