የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለሐረር ፌዴራል ፖሊስ ሆስፒታል እና አፓርትመንት ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውል የSupply and Fix CCTV and Data System ግዥ አስመልክቶ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/SF/51/2025
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለሐረር ፌዴራል ፖሊስ ሆስፒታል እና አፓርትመንት ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውል የSupply and Fix CCTV and Data System ግዥ አስመልክቶ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የዕቃው አይነት |
የፕሮጀክት ስም |
የጨረታ ቁጥር |
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
Supply and fix CCTV and Data System |
ሐረር ፌዴራል ፖሊስ ሆስፒታል እና አፖርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት |
DCE/SF/ 51/2025 |
የካቲት 26/2017 ዓ.ም 4፡00 |
የካቲት 26/2017 ዓ.ም 4፡15 |
300,000.00 |
ስለሆነም ፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይ ምዝገባ፣ የታደሰ ታክስ ክሊራንስ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አንድ ተጫራች መወዳደር የሚችለው በአንድ ዓይነት ምርት ሞዴል/ብቻ ነው:: በአማራጭ የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነዱ በተጠቀሰው ብዛት እና እስፔስፊኬሽን መሠረት መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ቃሊቲ ቶታል ከአዲሱ ስታዲየም ጀርባ ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዋና መ/ቤት የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የቀጥታ ቁጥር 0114-40-34-34
ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72
E-mail አድራሻ Info@dce-et.com
የድህረ ገፅ አድራሻ www.dce.gov.com/www.et.com
ፖ.ሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ. 0114-40-04-71/0114-42-07-46
ቃሊቲ ቶታል አዲሱ ስታዲየም ጀርባ ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
