የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2017 በጀት ዓመት የላቦራቶሪ ኬሚካሎች ግዥ የግዥው መለያ ቁጥር፡- ሃአግ/ባዳዩማግዥ/47/2017 ለሁለተኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ግዥ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Bahir Dar University (ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ)
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2017 በጀት ዓመት የላቦራቶሪ ኬሚካሎች ግዥ የግዥው መለያ ቁጥር፡- ሃአግ/ባዳዩማግዥ/47/2017 ለሁለተኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ግዥ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ-ገጽ (eGP) የተመዘገቡ፣ የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የሚገቡበት ቅፅ ላይ ማህተምና ፊርማ የተደረገበት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን፣ የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉና የግብር ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የድጋፍ ደብዳቤ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ማቅረብ የሚችሉ ሆነው ሁሉንም ሠነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒ በማድረግ እና የድርጅታቸውን ማህተም በማሳረፍ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በአግባቡ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ስም 1000013099522 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን የባንከ ደረሰኝ ከዩኒቨርሲቲው ፋይናንስ ክፍል የገቢ ደረሰኝ በማስቆረጥ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበብ ሕንፃ ማዕከላዊ ግዥ ክፍል G+2 ቢሮ ቁ-201 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለላቦራቶሪ ኬሚካሎች ግዥ ፡- የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 400,000.00 /አራት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፣ በባንክ በተረጋገጠ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ቢድ ቦንድ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ ለሚፈልጉ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስም 1000013099522 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን የባንክ ደረሰኝ ከዩኒቨርሲቲው ፋይናንስ ክፍል የገቢ ደረሰኝ በማስቆረጥ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አሽጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት በአዋጅ መሠረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ከአደራጃቸው ተቋም በጨረታ ማስከበሪያ የዋስትና ደብዳቤ ማስረጃ ዋናውን ደብዳቤ የሚወዳደሩበትን ሎት እና የብር መጠን በመጥቀስ ያለ ክፍያ በነፃ የጨረታ ሰነዱን እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች አሸናፊነቱ ታውቆ ውሉ ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ በውሉ መሠረት ማቅረብ የሚችል መሆን ይጠበቅበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለፅ ፖስታ ውስጥ አድርገው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ቀናት ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ሕንፃ ማዕከላዊ ግዥ ክፍል G+2 ቢሮ ቁ-201 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የላቦራቶሪ ኬሚካሎች ግዥ፡- ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ማሣሰቢያ ፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም ካላንደር የሚዘጋው ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይሆናል፡፡
- በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ዩኒቨርሲቲው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0583202052 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ
