በምሥ/ሸዋ ዞን የቦሰት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 Cinema chair ipported እና የውሃ ቧንቧ እና የቧንቧ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በምስራቅ ሸዋ ዞን የቦሰት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በምሥ/ሸዋ ዞን የቦሰት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 Cinema chair ipported እና የውሃ ቧንቧ እና የቧንቧ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤ ስለሆነም እጩ ተጫራቶች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ፈቃዳቸውን ያሳደሱ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሠነድ ከነዋጋ ማቅረቢያው በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮፒና ኦሪጅናል በመለት ይህ የጨረታ ማስታወቀያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታውም በ16ኛው ቀን ከቀኑ 6:00 ታሽጎ በዕለቱ በ 8፡00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም እጩ ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ ለማቅረብ በብሮሸር አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል፤ አስቀድሞ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ለመፈረም ፈቃደኛ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች በፌደራል ወይም በክልል ቢሮ አቅራቢዎች መዝገብ ላይ የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከቦሰት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጽ/ቤቱ ከቀረበው አጠቃላይ የግዢ ዋጋ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጠቅላላ የግዥ ዋጋ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ከሆነ 2% ተቀናሽ ይሆናል፤ እንዲሁም ክፍያው ከ20,000 (ሀያ ሺህ ብር) በላይ ለሆነ ግዥ 7.5 % ይቆረጣል፡፡
- እጩ ተጫራቾች የተጨማሪ ታክስ ከፋይ ወይም ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- የንግድ መለያ ቁጥር (TIN number) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች ካሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ካሸነፈ ከመ/ቤቱ ጋር ውሉን ከፈረመ በኋላ ዕቃውን ለቦሰት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በራሱ ማጓጓዣ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል፡፡
ስልክ ቁጥር ሥ.ቁ. 022 113-00-62
በምሥ/ሸዋ ዞን የቦሰት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
