የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2017 የበጀት ዓመት ካሜራ እና ለካሜራ ዝርጋታ የሚያስፈልጉ እቃዎችን የእጅ ዋጋ ጨምሮ ለሶስተኛ ጊዜ ለመግዛት ፣ እና ፎቶ ኮፒ፣ ፕሪንተር እና ፕሮጀክተር ሶስተኛ ዙር ለማስጠገን ማሰራት በግልፅ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።።
Adama Hospital Medical College (የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2017 የበጀት ዓመት :-
-
- ካሜራ እና ለካሜራ ዝርጋታ የሚያስፈልጉ እቃዎችን የእጅ ዋጋ ጨምሮ ለሶስተኛ ጊዜ ለመግዛት፣
- ፎቶ ኮፒ፣ ፕሪንተር እና ፕሮጀክተር ሶስተኛ ዙር ለማስጠገን ማሰራት በግልፅ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላለችሁ፡፡
- የ2017 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ በዘርፉ ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ ግዥ መ/ቤት ድረስ በራሳቸው ወጪ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ኮፒና ኦሪጅናል ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማሸግ አለባቸው።
- ስርዝ ድልዝ ያለው፤ የማይታይ የጨረታ ሰነድ ወይም የዋጋ ዝርዝር ተቀባይት የለውም፡፡
- ተጫራቶች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ የውል ማስከበሪያ የአሸነፉበትን ዋጋ 10% ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከኮሌጁ ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ክፍል ዘወትር በስራ ሰዓት ለካሜራ እና ካሜራ ዝርጋታ የሚያስፈልጉ እቃዎችን የእጅ ዋጋ ጨምሮ የማይመለስ ብር /200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ አለባቸው።
- የካሜራ እና ካሜራ ዝርጋታ የሚያስፈልጉ እቃዎችን የእጅ ዋጋ ጨምሮ ጨረታው የሚከፈተው በ19/06/2017 ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ነው::
- ኮፒ፣ ፕሪንተር እና ፕሮጀክተር ሶስተኛ ዙር ለማስጠገን/ለማሰራት ጨረታው የሚከፈተው በ19/6/2017 ከቀኑ 9፡30 ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ በመስሪያ ቤቱ ሰነድ ብቻ ላይ መሆን አለበት፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ለካሜራ እና ካሜራ ዝርጋታ የሚያስፈልጉ እቃዎችን የእጅ ዋጋ ጨምሮ 10,000 (አስር ሺህ) ብር እና ለፎቶ ኮፒ፣ ፕሪንተር እና ፕሮጀክተር ሶስተኛ ዙር ለማስጠገን/ለማሰራት ብር 10,000 (አስር ሺህ) ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ "በCBE, CBO, እና በSinqe ባንክ ብቻ ማስያዝ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022 812 39 56 ደውለው መረዳት ይችላሉ።
አዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ
