በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጌዴኦ ዞን የገደብ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ኢንሼቲቭ አካል የሆነው የገደብ ከተማ አስተዳደር አጥር ግንባታና የግሪኔር የፓይለት ፕሮጀክት ሥራ ግንባታ በዘርፉ በተሰማሩት ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ በደረጃ BC-4 እና ከዚያ በላይ በደረጃ Gር-5 እና ከዚያ በላይ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጌዴኦ ዞን የገደብ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 001/2017
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጌዴኦ ዞን የገደብ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ኢንሼቲቭ አካል የሆነው የገደብ ከተማ አስተዳደር አጥር ግንባታና የግሪኔር የፓይለት ፕሮጀክት ሥራ ግንባታ በዘርፉ በተሰማሩት ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ በደረጃ BC-4 እና ከዚያ በላይ በደረጃ Gር-5 እና ከዚያ በላይ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የግንባታ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፤
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ህጋዊ የሰውነት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
ከላይ በዝርዝር የተቀመጡትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሠነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ 500 ብር/አምስት መቶ ብር/ብቻ በመክፈል ሰነዱን ከገደብ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፤ ቫትን ያላካተተ ከሆነ ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
ተጫራቾች ጨረታ ማስከበሪያ ፡-
- ለፕሮጀክቱ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/CPO/፣ እና ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም በባንክ ዋስትና ሆኖ በጥሬ ገንዘብ ዋስትና ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ በተዘጋጀ ዝርዝር ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው አንድ ኦርጅናል ቴክኒካል ሰነድ እና ሁለት ኮፒ ቴክኒካል ሰነድ እንዲሁም አንድ ኦርጅናል ፋይናንሻል እና ሁለት ኮፒ በተለያዩ ፖስታ ካሸጉ በኋላ ከሲ.ፒ.ኦ. ጋር በአንድ ትልቁ እናት ፖስታ በስም በማሸግ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ማንኛውንም ዓይነት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ፤ ድልዝ ያለው ከሆነ በፊርማ ማረጋገጥ መኖር አለበት በእያንዳንዱ በጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ የድርጅት ማህተምና የተወካዩ ፊርማ መኖር አለበት፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይ ከዋለበት በተከታታይ የሥራ ቀናቶች በሚቆጠር 15 ቀናት በኋላ በ16ኛው በሥራ ቀን የጨረታ ሳጥን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች በዕለቱ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ የመወዳደሪያውን ሰነዶቻቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የሚመጡ ተጫራቾች ሰነድ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን ተጫራቾቹ በጨረታ መክፈቻ ዕለት የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመክፈት አያግድም። 16ኛ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ የሚገኘው በጌዴኦ ዞን በገደብ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ ቤት ቅጥር ግቢ ግዥና ንብ/አስ/ር ሥራ ሂደት ነው፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 10% የባንክ ጋራንት ማቅረብ የሚችል እና የቅድሜያ ክፍያ 10% ዋስትና ጭምር ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ:- በስልክ ቁጥር 09 26 501 488/09 26 060 263 መደወል ይቻላል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት
በጌዴኦ ዞን የገደብ
ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት
