በፋና ቦሌ ሸማቾች ኃላፊነቱ የተወሰነ ሕብረት ሥራ ማህበር የ17/17 ሕ/ል/ማእከል በ2017 ዓ.ም በዓመት ውስጥ ሊሠራቸው ካሰባቸው ስራዎች በሎት አንድ የቀረበውን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
በፋና ቦሌ ሸማቾች ኃላፊነቱ የተወሰነ ሕብረት ሥራ ማህበር የ17/17 ሕ/ል/ ማእከል
የጨረታ ማስታወቂያ
በፋና ቦሌ ሸማቾች ኃላፊነቱ የተወሰነ ሕብረት ሥራ ማህበር የ17/17 ሕ/ል/ማእከል በ2017 ዓ.ም በዓመት ውስጥ ሊሠራቸው ካሰባቸው ስራዎች በሎት አንድ የቀረበውን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የሎት ቁጥር |
የሥራው ዝርዝር |
|
1 |
ሎት 1 |
የኳስ ሜዳ፣ የቅርጫት ኳስ ስቴጅ እና የምንጣፍ ስራ |
ተጫራቾች ፡-
- በዘርፉ የታደሠ ህጋዊ የንግድ የሥራ ፈቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ወቅታዊ የግብር ክፍያ ማረጋገጫ፣ የቫት የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበ መሆን አለበት፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ CPO ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ሠነድ ሊወስዱ ሲመጡ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ሠነድ መግዛት ይኖርባቸዋል፤
- ከላይ የተዘረዘሩ መረጃዎችና ሰነዶች አሟልተው በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ እስከ 11፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በአስራ አንደኛው ቀን 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ሻላ 17/7 ህብረተሰብ ልማት ማዕከል ይከፈታል፡፡ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታ ሣጥን መክፈቻ ሥነ-ሥርዓትን አያስተጓጉልም፡፡
- አሻሚ፣ የተሰረዘ፣ የተደለዘ እና ግልፅ ባልሆነ ሁኔታ የጨረታ ዋጋ በመሙላት መወዳደር ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፤
- የጨረታውን መመሪያ አለማክበር ከጨረታው ያሰርዛል፤
- ፋና ቦሌ ሸማቾች ኃላ/የተ/የህ/ሥ/ማህበር ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ ፡- የፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/የህ/ሥራ ማህበር 17/17 ህብረተሰብ ልማት ማዕከል ሻላ መናፈሻ ቅጥር ግቢ ውስጥ የማዕከሉ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቀርበው ሠነዱን መግዛት ይቻላል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 0116 184 076/0116 187 529/0116 631 244
በፋና ቦሌ ሸማቾች ኃላፊነቱ የተወሰነ ሕብረት ሥራ ማህበር የ17/17 ሕ/ል/ማእከል
