በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል Surveillance Camera (item Supply, Installation and Trading) በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory (በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ)
የሀገር ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ሙሲፋ/43/2017
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል Surveillance Camera (item Supply, Installation and Trading) በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የንግድ ምዝገባና ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የ2017ዓ.ም፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የታክስ ከፋይ ተመዝጋቢ የሆኑ የተጠቀሱትን ኮፒ ሰነድ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100.00 ከቫት በፊት በመከፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በቅሎ ቤት አካባቢ ጋራድ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 432-38 ከሚገኘው የግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ። ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጠቅላላ ዋጋ 2% በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ስም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 09 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ጨረታው በዕለቱ መጋቢት 09 ቀን 2017 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል።
ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን
ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
ስልክ ቁጥር- 011 442 0216
ፋክስ 011 442 0688
አዲስ አበባ
