Tender Detail

Tender Details

  • Company Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory (በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ)
  • Address አዲስ አበባ በቅሎ ቤት አካባቢ ጋራድ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 432-3-8 ከሚገኘው የግዥ መምሪያ ቢሮ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114420688
  • Websitehttp://www.mughercement.com.et/
  • Deadline18 Mar 2025, 9:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Safety And Security

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለግቢ ውስጥ አገልግሎት የሚውል የሴፍቲ ምልክቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory (በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ)


 

የሀገር ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ሙሲፋ/Re-35/2017

 

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለግቢ ውስጥ አገልግሎት የሚውል የሴፍቲ ምልክቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የ2017ዒ.ም፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የታክስ ከፋይ ተመዝጋቢ የሆኑ የተጠቀሱትን ኮፒ ሰነድ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100.00 ከቫት በፊት በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በቅሎ ቤት አካባቢ ጋራድ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 432-3_8 ከሚገኘው የግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ። ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጠቅላላ ዋጋ 2% በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ስም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 09 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

ጨረታው በዕለቱ መጋቢት 09 ቀን 2017 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል። ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን

ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ

ስልክ ቁጥር 0114420216

ፋክስ 0114420688

አዲስ አበባ

 

Save Tender