በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ በቤንች ሸኮ ዞን የሰሜን ቤንች ወረዳ ፍርድ ቤት በ2017 ዓ/ም የበጀት ዓመት ግዥ ለመፈጸም ባቀደው መሠረት በመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ በቤንች ሸኮ ዞን የሰሜን ቤንች ወረዳ ፍርድ ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ በቤንች ሸኮ ዞን የሰሜን ቤንች ወረዳ ፍርድ ቤት በ2017 ዓ/ም የበጀት ዓመት ግዥ ለመፈጸም ባቀደው መሠረት በመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ማለትም፡-
- ኮምፒውተሮችን፤ የሳን-ቶፕ ኮምፒዉተሮችን እና ፕሮንቴሮችን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት
- በዘርፋ የተሰማሩበትን ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የዘመኑን ግብር ወይም 2017 በጀት አመት የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- በዕቃና አገልግሎት አቅራቢነት የተዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የያዘ ሰነድ (specification) ለሚጫረቱበት አይነት
- የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ እስከ 15/አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት ሰሜን ቤንች ወረዳ ፍ/ቤት በሚገኘው ግ/ክ/ነ/ለ/ር ቢሮ ቁጥር 100 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ --
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 5000 ብር /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ ክፍያ ማዘዣ ወይም cpo በሁኔታ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቼክ በሰሜን ቤንች ወረዳ ፍርድ ቤት ተብለው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ዋጋቸውን ሞልተው የሚያቀርቡት በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተጠቀሰው የዕቃዎች የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ (specification/ በሚለው የዕቃዎች ዝርዝር መሰረት ብቻ ይሆናል ::
- ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን በገዙት የጨረታ ሰንድ ሳይ ሞልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም አርፎበትና ተፈርሞበት በዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀኖች ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የተጫራቾች ተሟልተው አለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት ሥነ-ሥርዓት አያስተጓጉልም። መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 0917 061 693 /0913 459 602
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ በቤንች ሸኮ ዞን የሰሜን ቤንች ወረዳ ፍርድ ቤት
