Tender Detail

Tender Details

  • Company በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ት/ጽ/ቤት የየካ ቦሌ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 የካ ቦሌ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ልዩ ስሙ ጨሪ ሰፈር አንድሮሜዳ ት/ቤት ፊት ለፊት ባለው መንገድ 500 ሜትር ገባ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline23 Feb 2025, 10:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በአዲስ አበባ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 የካ ቦሌ ሁለተኛ/ደ/ት/ቤት ለ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የሁለተኛ ዙር ለስራ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ት/ጽ/ቤት የየካ ቦሌ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት


 

ግዥ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር 002/2017

 

በአዲስ አበባ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 የካ ቦሌ ሁለተኛ/ደ/ት/ቤት ለ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የሁለተኛ ዙር ለስራ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን ማለትም

ሎት 1 የፅህፈት ዕቃዎች፣

ሎት 2 የፅዳት እቃዎች

ሎት 3 የደንብ ልብስ

ሎት 4 ልዩ ልዩ መሳሪያ እቃዎች

ሎት 5 ቋሚ እቃዎች

ሎት 6 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።

  1. በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው።
  4. ቲን ነምበር ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
  5. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  6. ተጫራች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ C.P.O. ማቅረብ አለበት።

ሎት ቁጥር የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብር

ሎት 1 የጽህፈት እቃዎች ብር 6600.00

ሎት 2 የፅዳት እቃዎች ብር 2200.00

ሎት 3 የደንብ ልብስ  ብር 5000.00

ሎት 4 ልዩ ልዩ መሳሪያ እቃዎችብር 720.00

ሎት 5 ቋሚ እቃዎች ብር 3560.00

ሎት 6 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ብር 12120.00

  1. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 01 እየቀረቡ መግዛት ይቻላል።
  2. ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 01 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  3. ጨረታው በአስረኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 5፡00 ሰዓት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተሰጠው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  4. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋና የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው።
  6. የጨረታ አሽናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት መስሪያ ቤቱ ድረስ ማቅረብ አለበት።
  7. መ/ቤ/ቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 የካ ቦሌ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ልዩ ስሙ ጨሪ ሰፈር አንድሮሜዳ ት/ቤት ፊት ለፊት ባለው መንገድ 500 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል።

 

 

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ት/ጽ/ቤት የየካ ቦሌ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት

 

Save Tender