በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በሜካናይዝድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት ለስራ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግዥ ፍላጎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በሜካናይዝድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር A-03/2017
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በሜካናይዝድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት ለስራ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግዥ ፍላጎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
-
- የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎችና አላቂ መለዋወጫ እቃዎች እንዲሁም የዳቦ ማሽን መለዋወጫ
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፍርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ህጋዊ የሆነ ነጋዴ ተጫራች በጨረታው ሊወዳደር ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የጨረታ ዘርፍ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት፣ የቫት የምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የአቅራቢነት መታወቂያ ሰርተፊኬት እና ካለፉት 3 ወር የቫት ሪፖርት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን ያወዳድራል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ሰነዱ ላይ በተገለፀው የገንዘብ መጠን መሰረት በኢትዮጵያ ባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የዋጋ ማቅረቢያው ላይ በግልፅ ያለምንም ስርዝ ድልዝ በመፃፍ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነዱን ከተጫራቾች ዝርዝር መመሪያ ጋር የማይመለስ 250.00 ብር በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት የስራ ቀናት ውስጥ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ፊት ለፊት 200 ሜትር ዝቅ ብሎ ከሚገኘው የሜድ ዕዝ ጠ/ መምሪያ ግዥ ቡድን ቢሮ መግዛት ይቻላል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈፅሙ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና ከአሸነፉት ጠቅላላ ዋጋ 10% በኢ/ያ ባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ያሸነፉትን ዕቃ በራሳቸው ወጪ በማጓጓዝ እና በማራገፍ አዳማ የሜድ ዕዙ ጠ/መምሪያ ግምጃ ቤት ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማረጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው 24/6/2017 ዓም ከጠዋቱ 3፡30 ተዘግቶ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሜድ ዕዝ ቅጥር ግቢ ግዥ ቡድን ቢሮ አዳራሽ/ ውስጥ ይከፈታል።
- ስለሆነም የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዲታተምልን እየጠየቅን ማስታወቂያው እስከ 7/6/ 2017 ዓ/ም ታትሞ እንዲወጣልን በአክብሮት እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ. 09 11 043 690/9 11 025 079
ለሜካናይዝድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ግዥ ቡድን
አዳማ
