ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃዎች እና አገልግሎት በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አህስኮድ/ማሽግ 08/2017
ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃዎች እና አገልግሎት በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሀ. የGPS & GPRS/GSM አቅርቦት፣ ገጠማ፣ አሰራሩን የመከታተል እና ጥገና የመስጠት እንዲሁም ማኔጅመንት ሲስተም ኮሚሽኒንግ፤
ለ. የሪቬት መምቻ ማሽን (Brake pad rivet machine): የሆዝ መጭመቂያ (Hose crimping ma chine)፣ ፕረስ ማሽን (Press machine) የቸርኬ ማውጫ ማሽን (Tyre changer machine)፤ ፍሎር ጃክ (floor jack)፤ ቶርክ ሬንች (torque wrench)፣ ላሜራ መቁረጫ ማሽን (Sheet metal machine)፣ የቸርኬ ባላንስ ማሽን (Wheel balancer machine)፤ የጎማ መፍቻ (Impact wheel wrench) በኤሌክትሪክ የሚሰራ ሲሆኑ፤
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤
- በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤
- የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.አ (CPO) ወይም /unconditional bank guarantee/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
- የጨረታ ሰነዱን ባ/ዳር ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11 እና አ/አበባ ለገሀር አመልድ ኢትዮጵያ ህንጻ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ በ ሀ እና ለ ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል እና ፋይናንሽያል ሰነዶች ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን (15 ተከታታይ ቀናት በመቁጠር) ድረስ ብቻ በዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የማሽ/ተሽ/መ/ግዥና አቅ/ኬዝ ቲም ቢሮ (ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበብ ህንጻ አካባቢ የቀድሞው የአማራ ከተሞች ልማት አ.ማ ግቢ ውስጥ) በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ15ኛው ቀን በተራ ቁጥር 4 በተገለጸው ቦታ በ8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡ ፡ የመዝጊያና መክፈቻ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በዚያኑ ቀን 8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ዝርዝር የጨረታ መመሪያውን እና የውል ይዘቱን እንዲሁም የሚገዙትን እቃዎችና አገልግሎቶች፣ ዝርዝር ቴክኒካል መገምገሚያዎች በሙሉ ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተገለፀ ስለሆነ ማንኛውም ተጫራች በጥንቃቄ በማንበብ ዋጋቸውን በጨረታ መመሪያው መሰረት መሙላት አለበት፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር :- 058-320 5185/09 18 16 43 93/09 18 78 44 90: 4h:-058- 218-0538/058-320-4001
ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
