Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የጨፋ ሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
  • Address ጨፋ ሮቢት ከተማ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው መስመር 300 ኪ/ሜ ላይ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: +251913602313
  • Website
  • Deadline06 Mar 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የጨፋ ሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት በተራድኦ በጀት የሆስፒታል ፊኒሺንግ ሥራ ግንባታ ግዥ በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የጨፋ ሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2017

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የጨፋ ሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት በተራድኦ በጀት የሆስፒታል ፊኒሺንግ ሥራ ግንባታ ግዥ በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. ተጫራቾች ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ወይም ሕንፃ ሥራ ተቋራጭ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የታደሰ የብቃት ማረጋገጫና የመልካም ሥራ አፈፃፀም ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. በሚወዳደሩበት ዘርፍ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
  4. የTIN No ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የንግድ ምዝገባ ቁጥርና የተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  5. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው::
  6. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሀሳብ መስጫ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል።
  7. የጨረታው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
  8. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ሆኖ የጨረታ ማስከበሪያውን በመውረስ ለወደፊት በመንግሥት የሚወጣ ጨረታ ላይ እንዳይሳተፉ ሊደረግ ይችላል።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከዋና ገንዘብ ያዥ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. ተዛማጅ ወጪዎችን እንዲሁም የግብር እና የቀረጥ ወጭዎችን ጨምሮ መላውን ግንባታ ለመተግበር አስፈላጊ የሆነው ጠቅላላ ዋጋ በተመለከቱት የግንባታ አይነቶች ዝርዝር ዋጋ መሙያ መካተት አለባቸው።
  11. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመቀበያ ደረሰኝ በጨፋ ሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በምርጫቸው በአንዱ ከዋና /original/ የመወዳደሪያ ስነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን ብቻ ለብቻ ከሁሉም የንግድ ማስረጃዎቻቸው ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።
  13. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 6/6/2017 ዓ.ም እስከ 26/6/2017 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ ለ21 ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን 22ኛው ቀን ማለትም 27/6/2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት የሚታሸግ ይሆናል።
  14. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን ማለትም 27/6/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4:30 በጨፋ ሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 03 በግልጽ የሚከፈት ሲሆን ምናልባት 22ኛው ቀን የሕዝብ በዓል ወይም ከመንግሥት የሥራ ቀን ውጪ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  15. የጨረታ ማስገቢያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የመጣ የጨረታ ሰነድ ከጨረታ ሳጥን ውስጥ ሳይገባ ተመላሽ ይሆናል፡፡
  16. ተጫራቾች የሚሠራውን ሥራ በሆስፒታሉ በአካል ተገኝተው ተዘዋውረው ማየት ይችላሉ።
  17. መ/ቤቱ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251913602313/+251923064030 ደውሰው ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አድራሻን ጨፋ ሮቢት ከተማ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው መስመር 300 ኪ/ሜ ላይ እንገኛለን።

 

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የጨፋ ሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

 

Save Tender