በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በስልጤ ዞን የአሊቾ ዉሪሮ ወረዳ ፍርድ ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለሚያስገነባው የቢሮ ግንባታ በመስኩ የተሰማሩ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የስልጤ ዞን አሊቾ ዉሪሮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በስልጤ ዞን የአሊቾ ዉሪሮ ወረዳ ፍርድ ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለሚያስገነባው የቢሮ ግንባታ በመስኩ የተሰማሩ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ደረጃቸው G.C- 6/B.C-5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፣
- በተሰማሩበት ዘርፍ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና ስራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና ቲን ነበር ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
- የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ
- የኮንስትራክሽን እና ከተማ ልማት ሚኒስትር የዘመኑን የምዝገባ ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ
- የጨረታ ዋስትና 150,000 (አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ብር) ማስያዝ የሚችሉ
- የመስራት አቅም እንዳላቸው የሚገልፅ የወቅቱን የባንክ እስቴትመንት እና የስራ ልምድ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
- የኦዲት ሪፖርት እና የድርጅቱን አወቃቀር እና ከዚህ በፊት የሰራቸውን ስራዎች የሚገልፅ የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ ተቋራጮች ሰነዱን ከአሊቾ ዉሪሮ ወረዳ ፋይናንስ ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ ለሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት የሚችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻል ዶክመንቱን በሚገባ በመሙላት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ፤ ቴክኒካል ዶክመንቱን አንድ ኦርናጅል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 30 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የስራ ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ አሊቾ ዉሪሮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ በዚያው ዕለት 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ-
- ተጫራቾች ያቀረቡት የጨረታ ዋስትና ከተጠየቀው ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛሉ
- የተወዳዳሪ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ መክፈቻ ቀኑን አይለውጠውም
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታሙን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡ ስልክ ቁጥር 09-17-01-03-09/09-11-6483-46 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የስልጤ ዞን አሊቾ
ዉሪሮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
