የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሎት የተገለጹ የሶፍት ዌር ዕቃዎችና አገልግሎት እንዲሁም ሞተር ሳይክል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት
2ኛ ዙር የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ 07/2017
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሎት የተገለጹ የሶፍት ዌር ዕቃዎችና አገልግሎት እንዲሁም ሞተር ሳይክል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1. Bulk SMS system development, institution and testing
ሎት 2. Supply, installation, testing and communication of CCTV surveillance system
ሎት 3. ሞተር ሳይክል
በዚህ መሠረት
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፤ የዘመኑን ግብር የገበረ
- የቫት (VAT) ተመዝጋቢነት ሰርቲፍኬት ያለው
- የግብር ከፋይ (TIN) መለያ ቁጥር ያለው
- የእቃና የአገልግሎት አቅራቢነት ሰርቲፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶች
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሰውን ማስረጃዎችን አሪጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ለእያንዳንዱ ሎት ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) ብር ብቻ በሲዳማ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን በተከፈተው ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000347602028 በማስገባት ስሊፕ ይዞ ሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 208 በመቅረብ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) /BID BOND/ የ90 ቀን ለእያንዳንዱ ሎት ብር 10,000 (አስር ሺህ) ብር በጠቅላይ ፍርድ ቤት ስም በማሰራት ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቶች የፋይናንሻል ዶክመንት ኦሪጅናል 1 እና 2 ኮፒ በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፡ እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንት አሪጅናል 1 እና ኮፒ 1 በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ተከታታይ ቀናት ቅዳሜና ዕሁድን ጨምሮ ከ15 ቀን በኋላ በ16ኛ ቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ 8፡45 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።፡ ዕለቱ በዓል፣ ወይም የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ዕቃውን በራሱ ወጪ አጓጉዞ መጋዘን ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ በጨረታ መመሪያ መሠረት አሸናፊነቱ በማስታወቂያ ይገለጻል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡ ስልክ ቁጥር ፡- 0462125584/0939126096
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት
