የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የቴሌቪዥን ስቱዲዮ ሳውንድ ፕሩፍ ሥራ ከደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሕንፃ ሥራ ተቋራጮች እና ጠቅላላ ከነሙሉ እቃው የእጅ ዋጋን ጨምሮ በግለጽ ጨረታ ዘዴ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የቴሌቪዥን ስቱዲዮ ሳውንድ ፕሩፍ ሥራ ከደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሕንፃ ሥራ ተቋራጮች እና ጠቅላላ ከነሙሉ እቃው የእጅ ዋጋን ጨምሮ በግለጽ ጨረታ ዘዴ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ፤
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የብታት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ሰርተፍኬት፣ ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጠቅላላ ድምር ዋጋ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 21 /ሃያ አንድ/ ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 103 በመምጣት 200 /ሁለት መቶ/ ብር ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይቻላል፡፡ ሰነዱን በመሙላት የፋይናንስ ሰነዶችን ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነዶችን በጥንቃቄ በፖስታ ለየብቻ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተሞ፤ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እስከ 22ኛው ቀን 4:00 ድረሰ ማስገባት አለባቸው::
- ጨረታው በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ተዘግቶ በእለቱ ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ቢሮ ቁጥር 102 ይከፈታል፡፡ ነገርግን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በዕለቱ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ የተመሰከረለት ቼክ /ሲፒኦ/፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት 22ኛው ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ተዘግቶ 4:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ቢሮው ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የሚፈለጉት የቴሌቪዥን ስቱዱዮ ሳውንድ ፕሩፍ ስራዎች ዓይነት፣ ብዛትና ስፔስፊኬሽን እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት 4 ኪሎ ባሻ ወልዴ ኮንዶሚኒየም አልማ ህንጻ ቢሮ ቁጥር 102 ድረስ በመምጣት መውሰድ ይቻላል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09 18 72 07 21 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት
