የአድዋ የመጀ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ፣ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት አላቂ የትምህርት ዕቃ፣ አላቂ የቢሮ ዕቃ ፣ መጽሐፍትና መሳሪያዎች፣ ቋሚ ዕቃ መግዛትና ፤ የፓርትሽንና የበር ስራ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የአድዋ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የአድዋ የመጀ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ፣ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት አላቂ የትምህርት ዕቃ፣ አላቂ የቢሮ ዕቃ ፣ መጽሐፍትና መሳሪያዎች፣ ቋሚ ዕቃ መግዛትና ፤ የፓርትሽንና የበር ስራ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች በተገለፀው በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ (CPO) ከጨረታው ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸማ ማቅረብ የሚችሉ፣ ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት፡--
- ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ በዘርፉ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ በዘርፉ የተሰማሩ መሆን አለባቸው::
- ሎት 1- አላቂ የትምህርት ዕቃ ፣ ሎት 2- አላቂ የቢሮ ዕቃ ፣ ሎት 3- መጽሐፍትና መሳሪያዎች እና ሎት 4- ቋሚ ዕቃ 5000.00 /አምስት ሺህ ብር / ፤ ሎት 5 የፓርትሽንና የበር ስራ ደግሞ 12800.00 / አስራ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ (CPO) ከጨረታው ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 150.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል ሰነዱን በት/ቤቱ የፋ/ግ/ን/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 11፡30 ክፍት ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ አዳራሽ ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት የፋ/ግ/ን/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ቀን ለ60 ቀናት ነው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች በእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መሥሪያ ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- የጥቃቅን አነስተኛ ልዩ አስተያየት የሚያገኙት ባመረቱት ምርት እና በምርቱ ላይ እሴት በጨመሩት ብቻ ሲሆን ሌሎች እንደ ማንኛውም ተጫራች ሰነድ ገዝተው ወይም ሲፒኦ በማስያዝ ይወዳደራሉ፡፡
አድራሻ ፡- በን/ስ/ላ/ከ/ከ/ ወረዳ 06 መብራት ኃይል ኮንዶሚኒየም ግቢ ውስጥ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- 0114706943 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአድዋ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
