የቤ/ጉ/ክ/መ/ አሶሳ ዞን ሆሞሻ ወረዳ የሰራተኞች ደንብ ልብስ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ዞን ሆሞሻ ወረዳ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ መለያ ቁጥር 01/2017 ዓ/ም
የቤ/ጉ/ክ/መ/ አሶሳ ዞን ሆሞሻ ወረዳ የሰራተኞች ደንብ ልብስ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፣
- ተጫራቾች በዘርፉ የሥራ መስክ የታደስ የንግድ ስራ ፍቃድ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ማቅረብ የሚችሉ እና ከዕዳ ነፃ ስለመሆናቸው ከሚመለከተው አካል ታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የያዘ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በሆሞሻ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ክፍል በአካል በመቅረብ የዕቃው ዝርዝር መግለጫ እና የዋጋ መሙያ ሰነድ በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በመንግስት የግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የደንብ ልብሱን በራሳቸው ትራንስፖርት መ/ቤታችን ግቢ ማድረስ የሚችሉ ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ /Bid Bond/ ወይም ሲፒኦ /C.P.O/ ከኢት/ ብሔራዊ ባንክ እና እውቅና ካላቸው ባንኮች የተረጋገጠ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር / በጥሬ ማስያዝ የሚችሉ።
- የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚህ ዕለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት በሆ/ወ/ገ/ኢ/ል ጽ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የጨረታ የመክፈቻው ቀን በበዓላት ቀን ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ሳምፕል ወይም ናሙና በተጠየቀው መስፈርት መሰረት ስለሆኑ ለማረጋገጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው::
- ማንኛውም ተጫራች የዕቃውን ሳምፕል/ናሙና በተጠየቀው እስፔስፊኬሽን መሰረት ካልቀረበ ከጨረታው ውጭ ይደረጋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነወ።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0922 18 39 16/0923542541
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ዞን
ሆሞሻ ወረዳ
