አርባ ምንጭ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት ለኮሌጃችን ሥራ አገ/ት የሚውሉ ሎት-1- የጽህፈት መሳሪያ ግዥ እና ሎት-2- የላቦራቶሪ ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Arba Minch College of Health Science (የአርባ ምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ
አርባ ምንጭ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት ለኮሌጃችን ሥራ አገ/ት የሚውሉ
ሎት-1- የጽህፈት መሳሪያ ግዥ
ሎት-2- የላቦራቶሪ ዕቃዎች ግዥ
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም አቅራቢዎች ከላይ በተጠቀሱና ተዛማጅ የንግድ ዘርፎች የተሰማሩ መሆን የሚገባቸው ሆነው ሁሉም አቅራቢዎች :-
- ህጋዊ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ
- በአቅራቢነት ዝርዝር ላይ የተመዘቡ
- የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት
- የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት (Tin number)
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን ዝርዝር ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ ከአርባ ምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር - 7 የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በየሎቱ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ሰነዳቸውን ዋጋ በመሙላት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ አርባምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር -7 ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጐ በ8፡30 በአርባ ምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መሰብሰብያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 16ኛ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረ /CPO/ ሲፒኦ ወይም Bid bond ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ውጤት የጨረታ አናሊሲስ ተሰርቶ እንዳበቃ አርባምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በማስታወቂያ ይገልጻል፡፡
- ለተሸናፊ ተጫራቾች /CPO/ ሲፒኦ ተመላሽ የሚደረገው ከኮሌጁ አሸናፊውን ተጫራች ለይቶ በማስታወቂያ ካሳወቀ እና ውል ከገባ በኋላ ይሆናል፡፡
- ለአሸናፊ ተጫራቾች /CPO/ ሲፒኦ ተመላሽ የሚደረገው ከኮሌጁ ጋር የአቅርቦት ውል ከፈፀሙና እቃዎችን ካቀረቡ በኋላ ነው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ሰነዶች አንድ ኦርጂናል አንድ ፎቶ ኮፒ አንዳንድ በተለያየ በታሽገ ኤንቬሎፕ ውስጥ ሆኖ ማህተምና ፊርማ ተደርጎባቸው ሁለቱንም ፖስታዎች በአንድ ሌላ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በሰም ታሽጎ መቅረብ አለበት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ በኦርጅናል ፖስታ ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0468812572/0468810493 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአርባ ምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
