የደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መ/ህብረት ስራ ልማት ኤጀንሲ በ2017 በጀት ዓመት የአፈር ማዳበሪያ ሽያጭ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ (ኩፖን) እና የማህበራት እድሳት ሠርተፊኬት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መ/ህብረት ስራ ልማት ኤጀንሲ በ2017 በጀት ዓመት የአፈር ማዳበሪያ ሽያጭ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ (ኩፖን) እና የማህበራት እድሳት ሠርተፊኬት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ፡-
- አቅራቢው የተሰማራበትን የስራ ዘርፍ የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፤
- የዘመኑን ግብር መክፈሉን የሚገልፅ ማስረጃ!
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤
- ከተሰማሩብት ዘርፍ ጋር በተያያዘ ስለተሰማሩብት የሙያ ዘርፍ አቅራቢነት በሚመለከተው አካል የተሰጠ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10000 (አስር ሺህ ብር) በሁታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በማይሻር ሌተር ኦፍ ክሬዲት የቀረበ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ወይም ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም የክፍያ ትዕዛዝ ህጋዊ ማህተም ያለው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ የሆነው ተጫራች ለውል ማስከበሪያ የሚሆን በቂ ዋስትናና ለዋስትና ሊያበቁ የሚችሉ ማስያዣዎች 10% ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመያዝ ደ/ምዕ/አ/ሕ/ክ/መ/ ህብረት ስራ ልማት ኤጀንሲ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል ቀርበው በመክፈል ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃን።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ሲመጡ በዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የፋይናንሻልና የቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ በመለየት በተለያዩ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሠዓት ታሽጎ በዛው ዕለት በ4፡30 ሠዓት የሚከፈት ሲሆን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በግልፅ ይከፈታል፡፡
- የሚታተመውን የደረሰኝ ዓይነት /ናሙና/ ቢሮ መጥተው ማየት (የራሳቸውን ናሙና ማቅረባ ይችላሉ)፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የታተሙትን ደረሰኞች የክልሉ ህብረት ስራ ኤጀንሲ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- 047-1-35-04-18 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መ/ህብረት
ስራ ልማት ኤጀንሲ
