ድርጅታችን የተለያዩ ብረታ ብረቶች ፣ አሮጌ የቢሮ ዕቃዎች፣ አሮጌ የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች እና የፋብሪካ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሸገር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር :- OFWE 05/2017
ድርጅታችን የተለያዩ ብረታ ብረቶች ፣ አሮጌ የቢሮ ዕቃዎች፣ አሮጌ የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች እና የፋብሪካ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በዘርፉ ላይ የተሰማራችሁ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሠነዱን ከድርጅታችን መግዛት የምትችሉ ሲሆን ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው።
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ እና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እና የሥራ መለያ ቁጥር ቲን ቁጥር ያላቸውና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራች ድርጅቶች የጨረታ ማስከበሪያ የተጫረቱበትን ከጠቅላላ ዋጋ 5% በCPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሸገር ቅርንጫፍ በሚል ስም በማሰራት ማቅረብ የሚችሉ።
- ማንኛውም ተጫራች ሌላው ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
- ከጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት ካለፈ ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የጨረታ ሠነዱን ለቡ መብራት ኃይል ሮያል ከረሜላና ቸኮሌት ፋብሪካ ህንጻ 3ተኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘው ቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን ከሰኞ እስከ አርብ በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ። ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በበ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ ይችላል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- 09-12-08-02-21/ 09-12-13-17-95 መጠየቅ ይቻላል።
በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት የሸገር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
