ጽ/ቤታችን በ2017 ዓ.ም ሊገዙ የታቀዱ ግዥዎች ውስጥ አንዱ የሰራተኛ ደንብ ልብስ፣ የአነስተኛ የመኪና ተሽከርካሪ ጎማ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በቤ/ጉ/ክ/መ/ በአሶሳ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ የቡልድግሉ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ጽ/ቤታችን በ2017 ዓ.ም ሊገዙ የታቀዱ ግዥዎች ውስጥ አንዱ የሰራተኛ ደንብ ልብስ፣ የአነስተኛ የመኪና ተሽከርካሪ ጎማ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በዚህ ዘርፍ ለተሰማሩ ድርጅቶች የሚከተለውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፤
- የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከቤ/ጉ/ክ/መ/ገ/ኢ/ል/ቢሮ በመምጣት የማይመለስ ለሎት 1. ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ፤ ለሎት 2. ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ ከፍለው መውሰድ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የዋጋ 2% ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
- ለአሸናፊ ድርጅቶች ክፍያ የሚፈጸመው ውል ለተገባባቸው ዕቃዎች ቤ/ጉ/ክ/መ/ገ/ኢ/ል/ቢሮ ላይ ዕቃዎችን ሲያስረክብ ከፍያውም ጽ/ቤታችን በሚወከለው ሰራተኛ ካስገቡ በኋላ ነው፡፡
- ተጫራቾች ኮፒ እና ኦሪጅናል ሙሉ ማስረጃቸውን እንድታቀርቡ እየገለጽን ይህ ማስታዋወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሠነዱንና የውል ስምምነቱን በመግዛት በፖስታው ላይ ሕጋዊ ማህተም በማድርግ እና በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ ለተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው ቀን ሎት 1. በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚህ ቀን በ4፡30 ሰዓት ላይ በቤ/ጉ/ክ/መ/ገ/ኢ/ል/ቢሮ ግቢ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻች በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እያሳወቅን ለሎት 2 ከሰዓት በኋላ 9፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከሰዓት በኋላ 9፡30 ሰዓት ላይ ቤ/ጉ/ክ/መ/ገ/ኢ/ል/ቢሮ ግቢ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- የጨረታው መዝጊያ እና መከፈቻ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09-22-22-89-95/ 09-17-42-94-45
በቤ/ጉ/ክ/መ/ በአሶሳ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ የቡልድግሉ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
