አልፋ የትምህርትና ሥልጠና አክሲዮን ማህበር አልፋ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ብዛት ያላቸው የተለያዩ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎችና የፅዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
አልፋ የትምህርት ሥልጠና አክስዮን ማህበር (ALPHA Education and Training Share Company)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር-01/2017
አልፋ የትምህርትና ሥልጠና አክሲዮን ማህበር አልፋ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ብዛት ያላቸው የተለያዩ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎችና የፅዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ፡-
• ሎት አንድ :- የተለያዩ አይነት የጽህፈት መሣሪያዎች፣
• ሎት ሁለት :- የተለያዩ አይነት የፕሪንተር ቶነሮች፣
• ሎት ሶስት :- የተለያዩ አይነት የፅዳት ዕቃዎች፣
- ህጋዊ የታደሰ የዘመኑ የንግድ ሥራ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬትና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው (ማቅረብ የሚችሉ)፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ካቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነድ ጋር በመያያዝ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ ለ10 (እሥር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ከነቫቱ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ቢሮ ቁጥር 04 ገንዘብ ቤት እየከፈሉ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት ቢሮ ቁጥር 7 የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ በ10ኛው ቀን በ8:00 ሰዓት ታሽጎ በ8:15 ሰዓት ላይ በሴኔት አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቧቸውን ዕቃዎች ኦሪጅናል ናሙና ጨረታ ከመውጣቱ አስቀድሞ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በተጨማሪ ዝርዝር አፈፃፀሙ በጨረታ ሰነድ ውስጥ ይገለፃል፡፡
- አከሲዮን ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር ፡- 011-4-66-66-11/ 011-4-66-96-38
አድራሻ ፡- አራት ኪሎ ወወክማ አጠገብ
አልፋ የትምህርትና ሥልጠና አክሲዮን ማህበር
