Tender Detail

Tender Details

  • Company አበበች ጎበና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
  • Address ዮሐንስ ጸበል አካበቢ ወደ አቤት ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ወደ ውስጥ በሚያስገባው, Phone: 0118126317
  • Website
  • Deadline15 Feb 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Materials

አበበች ጎበና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ2017 ዓ.ም በጀት አመት የተለያዩ በሎት ምድብ የተከፋፈሉ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

አበበች ጎበና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት


 

የ3ኛ ዙር ገልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግል መለያ ቁጥር አበበች ጎበና የመ/ደ/ት/ቤት 03/2017 ዓ.ም

 

አበበች ጎበና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ2017 ዓ.ም በጀት አመት የተለያዩ በሎት ምድብ የተከፋፈሉ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ሎት 1- አላቂ የቢሮ እቃዎች

ሎት 2- አላቂ የህክምና እቃዎች

ሎት 3- አላቂ የጽዳት እቃዎች

ሎት 4- አላቂ ዝቅተኛ ቋሚ እቃዎች

ሎት 5- ለሕንፃ፤ ለቁሳቁስ እና ለተግጣጣሚዎች ቋሚ እቃዎች

ሎት 6- ጥገና አገልግሎቶች

ስለሆንም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. በዘርፉ የተሰማሩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉ መሆናቸውንና በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚቸሉ፡፡
  2. በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ የንግድ ምዝገባ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. በመንግስት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ከላይ የተጠቀሱትን እድሳትና ጥገና ዝርዝር የሚያሳውቅ የግዥ የግልጽ ጨረታን የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት አበበች ጎበና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ፋይናንስና ግዥ ቢሮ ቁጥር 1 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ለጨረታ ማሰረከቢያ የሚያገለግል የሚወዳደሩበትን 2% በት/ቤቱ ስም በተዘጋጀው ሲፒኦ ብቻ ከኦርጅናል ማስረጃ ፖስታ ውስጥ ሲፒኦ በማድረግ በመያዝ ማረጋገጫውን ከሚወዳደሩበት ሰነዶቻቸው ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም ጨረታውን ካሸነፉ ደግሞ የውል ማስከበሪያ የሚሆን ያሸነፉበት የገንዘብ መጠን 10% ሲፒኦ ብቻ በማሰራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ለውል ማስከበሪያ አያገለግልም፡፡
  6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን መስሪያ ቤቱ ባቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር ላይ የአንዱ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላት የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በአበበች ጎበና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ለዚሁ ጨረታ ሰነድ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድና ለመወዳደር የሚያስፈልጉ ዝርዝር ሰነዶች ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
  8. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለሁሉም እቃዎች የቅርብ ጊዜ ምርት (ጊዜው ያላለፈበት ምርት) ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ ለአንድ እቃ አንድ ናሙና መቅረብ አለበት፡፡
  9. ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ማህተም በማድረግ በታሸገ ካኪ ፖስታ ሳጥን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው በ26/5/2017 ዓ.ም እስከ 7/6/2017 ዓ.ም ድረስ በ11ኛው የስራ ቀን 8/6/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም አበበች ጎበና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ይከፈታል፡፡
  11. ጥቃቅንና አነስተኛ እራሳቸው አምራችና የሀገር ውስጥ ምርት የሚያቀርቡ ከሆኑ ልዩ አስተያየት ይደረግላቸዋል፡፡ በተጨማሪም ወደኛ ሰነድ ለመውሰድ ስትመጡ አምራች ስለመሆናችሁና የሀገር ውስጥ ምርት መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ አለባችሁ፡፡ ነገር ግን አምራችና የሀገር ውስጥ ምርት አቅራቢ ካልሆናችሁ እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ መግዛትና ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪ መወዳደር የሚችሉት በተደራጁበት ዘርፍ ላይ ብቻ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  12. ማንኛውም ተጫራች በተዘጋጀው ሰነድ ነው ሞልቶ ማቅረብ የሚቻለው ከዚያ ውጪ ለሚያመጣ ውድቅ ይደረጋል፡፡ በተጨማሪም ማንኛውም ተጫራች የተዘጋጀውን ሰነዱን ሙሉ ለሙሉ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
  13. ትምህርት ቤቱ የተሻለ የግዢ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 

ለበለጠ መረጃ አድራሻችን ፡- ዮሐንስ ጸበል አካበቢ ወደ አቤት ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ወደ ውስጥ በሚያስገባው ወይም በተለምዶ አይሻ መስጊድ አጠገብ

ስልክ ቁጥር ፡- 0118126317

 

አበበች ጎበና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት

 

Save Tender