Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት
  • Address ሶዶ : ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0461804426
  • Website
  • Deadline22 Feb 2025, 3:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በስሩ ላሉ የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራ ፕሮጀክቶች /በመደበኛ፤ በኤስ ዲ ጂ እና በመንገድ ፈንድ/አገልግሎት የሚሆኑ የአርማታ ፌሮ ብረት ባለ 6∅  ፤ ባለ 8∅  ፤ ባለ 10∅  ፤ ባለ 12∅  ፤ ባለ 14∅  ፤ ባለ 16∅  ፤ ባለ 20∅  እና ባለ 24∅  ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ሶዶ ዲስትሪክት 002/2017

 

በደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በስሩ ላሉ የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራ ፕሮጀክቶች /በመደበኛ፤ በኤስ ዲ ጂ እና በመንገድ ፈንድ/አገልግሎት የሚሆኑ የአርማታ ፌሮ ብረት ባለ 6∅  ፤ ባለ 8∅  ፤ ባለ 10∅  ፤ ባለ 12∅  ፤ ባለ 14∅  ፤ ባለ 16∅  ፤ ባለ 20∅  እና ባለ 24∅  ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ፡-

  1. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ የስራ ወይም የአገልግሎት የስራ ፈቃድ ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የአርማታ ብረት በኢትዮጵያ ደረጃዎች ወይም /S360/ የሆነ ደግሞ የዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃ /ISO/ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሠነዳቸው ጋር አብሮ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንስ ፕሮፖዛሉን በተለያየ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና እና አንድ ኮፒ “ኦርጅናል” እና “ኮፒ” በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያ በተለያየ ፖስታ ለብቻው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የአርማታ የብረት ዓይነትና የት ሀገር ምርት እንደሆነ እንዲሁም ግሬዱን ለይተው በጨረታ መወዳደሪያ ሠነዱ ላይ መግለጽ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ደ/ኢ/መ/ባ/ሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።
  6. የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሠነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው መስፈርቱን ለሚያሟላ ማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው።
  7. አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ይሆናል። ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
  8. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሠነድ ላይ በተቀመጠው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
  9. ተጫራቾች በጨረታ ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው ፤ ከደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
  10. ዲስትሪክቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046-1-80-44-26 ሶዶ ዲስትሪክት ፋይናንስና ሎጅስቲክስ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

ደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት

 

Save Tender