የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምስራት ዕዝ ጠ/መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት ለዕዙ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የደንብ ልብስ፣ አላቂ ዕቃዎች ፤ የትምህርት መርጃ ዕቃዎች ፤ የፅዳትና ሌሎች አቅርቦቶች፤ የግንባታ ዕቃዎች ፤ የተሽከርካሪና የጀነፌተር መለዋወጫዎች፤ የማሽነሪና ኤሌክትሮኒክስ መለዋወጫ ዕቃዎች ፤ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ፈርኒቸሮች የኤሌክትሪክ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በኢፌዱሪ መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ጠ/መምሪያ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር መከ/ሰ/ምስ/ዕዝ/ግ/ጨ/02/2017
የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምስራት ዕዝ ጠ/መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት ለዕዙ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የደንብ ልብስ፣ አላቂ ዕቃዎች ፤ የትምህርት መርጃ ዕቃዎች ፤ የፅዳትና ሌሎች አቅርቦቶች፤ የግንባታ ዕቃዎች ፤ የተሽከርካሪና የጀነፌተር መለዋወጫዎች፤ የማሽነሪና ኤሌክትሮኒክስ መለዋወጫ ዕቃዎች ፤ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ፈርኒቸሮች የኤሌክትሪክ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች ፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ አቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡና በጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክሰ እና የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ጨረታው የሚከናወነው በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ፈዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ባወጣው የመንግሥት ግዥ አዋጅ መሠረት ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች ነው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የተሟሉና በአማርኛ የተዘጋጁ ሰነዶችን በተራ ቁጥር 6/ሀ/ በተገለፀው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የጨረታው ሰነድ የሚላከው በተጫራቾች ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸው ሲሆን ሰነዱ ቢጠፋ ወይም ቢዘገይ ኃላፊነቱን የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች በተ.ቁ 6/ሀ/ በተገለፀው አድራሻ እስከ 17/6/2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ለሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ፋይናንሻልና ቴክኒካል እንዲሁም አርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 17/6/2017 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ከታወቀ ባንከ በሲ.ፒ.ኦ ከሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 6/ሀ/ በተገለፀው አድራሻ በ 14/6/2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያና ሰነድ ማስገቢያ ፡-
ሀ/ ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄ ፡- ዘወትር በሥራ ሰዓት በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ሠመራ ከተማ የሰሜን ምስ/ዕዝ/ፋይ/ሥራ/አመ ዘርፍ ግዥ ክፍል ቢሮ
• ስልክ ቁጥር፡- 0945593089/0991454479
ለ/ የሰነዱ ሽያጭ የሚከናወንበት አድራሻ ፡- በተ/ቁ 6/ሀ/ ላይ ይመልከቱ፡፡
ሐ/ ጨረታው የሚላክበት አድራሻ ፡- በተ/ቁ 6/ሀ/ ላይ ይመልከቱ፡፡
መ/ ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ ፡- በተ/ቁ 6/ሀ/ ላይ ይመልከቱ፡
ሠ/ ንብረቱ ገቢ የሚሆነው ፡- ሠመራ ከተማ ሰሜን ምስራቅ ዕዝ ን/ግ/ቤት ነው፡፡
ዕዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
በኢፌዱሪ መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ጠ/መምሪያ
