Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ሐዋርያት ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0113430173
  • Website
  • Deadline28 Feb 2025, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Water Construction

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ውሃ ማእድንና ኢነርጂ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በውርአንፉና ቀበሌ የውሃ አቅርቦት ለማድረግ በዘናበነር ቀበሌ ካለው ነባር የጥልቅ ጉድጓድ ማስፋፊያ 50 ሜትር ኪዩብ የውሃ ማጠራቀሚያ ታንከር ግንባታ፤ አንከር ብሎክ እና የፕሬዠር መስመር ዝርጋታ ከነባሩ የውርእንፉና መስመር የሚያገናኝ ስራ እንዲሁም በመቆርቆር ቀበሌ የውሃ አቅርቦት ለማድረግ ካለው ነባር የጥልቅ ጉድጓድ ማስፋፊያ ቦኖ ፣ እስታንድ ባይ ግንባታ እና የመስመር ዝርጋታ ስራ ለማሰራት ህጋዊ ተጫራቶችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር-0001

 

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ውሃ ማእድንና ኢነርጂ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በውርአንፉና ቀበሌ የውሃ አቅርቦት ለማድረግ በዘናበነር ቀበሌ ካለው ነባር የጥልቅ ጉድጓድ ማስፋፊያ 50 ሜትር ኪዩብ የውሃ ማጠራቀሚያ ታንከር ግንባታ፤ አንከር ብሎክ እና የፕሬዠር መስመር ዝርጋታ ከነባሩ የውርእንፉና መስመር የሚያገናኝ ስራ እንዲሁም በመቆርቆር ቀበሌ የውሃ አቅርቦት ለማድረግ ካለው ነባር የጥልቅ ጉድጓድ ማስፋፊያ ቦኖ ፣ እስታንድ ባይ ግንባታ እና የመስመር ዝርጋታ ስራ ለማሰራት ህጋዊ ተጫራቶችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ፡-

  1. GC/WC ደረጃ 6 እና ከዛ በላይ የታደሰ የግንባታ ፍቃድ ያላችሁ፤
  2. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፤ የንግድ ምዝገባ ፍቃድ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ፤ የተ.እታ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በም/አ/ወ/ገ/ጽ/ቤት የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ/ፅ/ቤት ግዢ ቢሮ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ CPO ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ) በምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማሰራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው በኦሪጅናል ዶክመንት ውስጥ መሆን ይኖርበታል፡፡
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ኦርጅናልና ሁለት ቅጂ ሰነዶችን በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሃያ አንደኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ አላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማቆያ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  6. ጨረታው በሃያ አንደኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታው እንዳይከፈት አያደርግም፡፡
  7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይተላለፋል፡፡
  8. ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ፡- 0113430173/0113430614 ይደውሉ

 

በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

ሐዋሪያ

Save Tender