በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማና በዙሪያ ለሚገኙ ነዋሪዎች ለሁሉም ክፍለ ከተሞች ጤና መድህን ተጠቃሚዎች፣ ለፌደራል ጤና መድህን ተጠቃሚዎች፣ በመንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጥራትና ፈዋሽነታቸው የተረጋገጡ መድኃኒቶችና የህክምና መገልገያዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ በ53 መድኃኒት ቤቶች የዱቤ /Credit/ እና ጥሬ ገንዘብ /Cash/ ሽያጭ አገልግሎት እየሰጠ ያለ የመንግስት የልማት ድርጅት ነው። ስለሆነም የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት እንዲያስችለው መድኃኒቶችን በግልፅ ጨረታ በውል ስምምነት ማቅረብ የሚችሉ ብቁ የሆኑ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
Kenema Pharmacy Enterprise (ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 007/2017
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማና በዙሪያ ለሚገኙ ነዋሪዎች ለሁሉም ክፍለ ከተሞች ጤና መድህን ተጠቃሚዎች፣ ለፌደራል ጤና መድህን ተጠቃሚዎች፣ በመንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጥራትና ፈዋሽነታቸው የተረጋገጡ መድኃኒቶችና የህክምና መገልገያዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ በ53 መድኃኒት ቤቶች የዱቤ /Credit/ እና ጥሬ ገንዘብ /Cash/ ሽያጭ አገልግሎት እየሰጠ ያለ የመንግስት የልማት ድርጅት ነው። ስለሆነም የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት እንዲያስችለው መድኃኒቶችን በግልፅ ጨረታ በውል ስምምነት ማቅረብ የሚችሉ ብቁ የሆኑ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- በንግድ ዘርፉ ወይም በመስኩ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱና የቲን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የታደሰ የዳካ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ/ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት/ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ/ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ ኤስ ኤም ኤስ ኤስ/SMSS/ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ማስገባት የሚቻል ሲሆን 4፡30 የጨረታው ሳጥን የሚታሸግ ስለሆነ አርፍዶ የሚመጣ ተቀባይነት የለውም። በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች /ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ሳጥን በድርጅቱ ግዥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ክፍል 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 የሚከፈት ይሆናል።
ማሳሰቢያ ፡- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ከፒያሳ ወደ አዲሱ ገበያ በሚወስደው መንገድ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ ኤስ ኤም ኤስ ኤስ /SMSS/ ህንፃ
የስራ ሰዓት ፡- ከሰኞ-አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ቅዳሜ 2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ፡ 0118578696
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት
