የመንቆረር ኮንስትራከሽን ኢንተርፕራይዝ በአማራ ከልል በምስራቅ ጎጃም ዞን በደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መንግስታዊ የሆነ የልማት ድርጅት ሲሆን ለክሬሸር ፕላንት ጠጠር ግብዓት አቅርቦትና ፍንዳታ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
Menkorer Construction Enterprize (የመንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ)
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- መኮ/ሎጅ/692/ጨ-01
የመንቆረር ኮንስትራከሽን ኢንተርፕራይዝ በአማራ ከልል በምስራቅ ጎጃም ዞን በደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መንግስታዊ የሆነ የልማት ድርጅት ሲሆን ለክሬሸር ፕላንት ጠጠር ግብዓት አቅርቦትና ፍንዳታ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ፡-
- ተጫራቾች የምትጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 7 ማስገባት አለባችሁ፡፡
- ጨረታው የጨረታ ማስገቢያው በተጠናቀቀ በቀጣይ ቀን በ3፡00 ሰዓት ታሽጎ በ3፡30 ሰዓት ላይ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በበዓላት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሆኖም በራሳቸው ፈቃድ በመክፈቻው ቀን ባይገኙ የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የተመዘገቡና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የነጋዴነት መለያ ቁጥር፤ የዘመኑን ግብር የገበሩና የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 11 ድረስ በመቅረብ 200.00 /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የፋይናንሽያል ኦሪጅናል ሰነዶችን በጥንቃቄ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠ/ዋጋ 2% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የሚሰራቸው የፈንጅ ፍንዳታ ስራ በተቀመጠለት ዝርዝር መሰረት በባለሙያ ተረጋግጠው ማለፍ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ 10% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን የፈንጅ አቅርቦትና ፍንዳታ ስራ በራሱ ትራንስፖርት ሙሉ ማቴሪያል አቅርቦ ደ/ማርቆስ ከተማ ክሬሸር ፕላንት በማቅረብ ማፈንዳት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ባሉት 7 /ሰባት/ የስራ ቀናት ውስጥ ውል መያዝ አለባቸው፡፡
- ኢንተርፕራይዙ የተሻለ መንገድ ወይም አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ - 09-62-28-68-40 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በምስ/ጎጃም ዞን በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር
የመንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
