Tender Detail

Tender Details

  • Company በወላይታ ዞን ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት
  • Address ወላይታ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0465599446
  • Website
  • Deadline09 Mar 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Agriculture And Farming

በደ/ኢ/ክ/መ/ በወላይታ ዞን ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 ዓ.ም ለግብርና ጽ/ቤት በሴፍቲኔት -5 ፕሮግራም በጀት የተለያዩ የጓሮ አትክልት ዘርና ችግኝ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በወላይታ ዞን ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደ/ኢ/ክ/መ/ በወላይታ ዞን ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 ዓ.ም ለግብርና ጽ/ቤት በሴፍቲኔት -5 ፕሮግራም በጀት የተለያዩ የጓሮ አትክልት ዘርና ችግኝ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ የንግድ ሥራ ድርጅቶች፣

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፤
  2. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
  3. የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የቲን ተመዝጋቢ የሆነ፣
  4. የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  5. የግብርና ጥራትና ቁጥጥር ኳራንታይን ባለስልጣን የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
  6. አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ዕቃውን እስከ አጫራች መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ የሚችል፡፡
  7. የጨረታ ማስከበሪያ በማንኛውም ባንክ የተመሰከረለት ብር 30,000 /ሠላሳ ሺህ/ ብር ብቻ በሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ የሚችል፡፡
  8. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከዳሞት ፑላሳ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በቢሮ ቁጥር 04 የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና የኦርጅናሉ አንድ ፎቶ ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውንና የድርጅቱን ስም በመጥቀስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. በጨረታው አሸናፊ ከሆኑ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ የሚችሉ፣
  11. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 30 /ሠላሳ/ በተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው በ31ኛው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 በዳ/ፑ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቀጥር 04 ይከፈታል፡፡
  12. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ከበሽታና ከተባይ ነፃ የሆነ የፍራፍሬ ችግኝና ዘር ማቅረብ የሚችል፡፡
  13. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የነጠላ ዋጋ የማይነበብና ስርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም፤

 

ማሳሰቢያ፣ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ 0468932510 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

 

በወላይታ ዞን ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት

 

Save Tender