Tender Detail

Tender Details

  • Company በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address አራት ኪሎ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ፋይናንስ ጽ/ቤት ዳብር ህንጻ ፊት ለፊት ብርሃንና ሰላም አለፍ ብሎ ቡና ባንክ አጠገብ፡፡ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-8-68-47-83
  • Website
  • Deadline16 Feb 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 9 አስተዳደር ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በ2ኛ ዙር ጨረታ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የጽህፈት መሳሪያና የጽዳት እቃዎች የደንብ ልብስ ስፈት፡ የጓሮ አትክልት ዘር በ2ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድረን መግዛት እንፈልጋለን፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ፡- 02/2017

 

በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 9 አስተዳደር ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በ2ኛ ዙር ጨረታ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የጽህፈት መሳሪያና የጽዳት እቃዎች የደንብ ልብስ ስፌት፡ የጓሮ አትክልት ዘር በ2ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድረን መግዛት እንፈልጋለን፡፡

በዚህ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ፡-

  1. በዘርፉ አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን ነምበር፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው።
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. በተጨማሪ ተጫራቾች በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን (መመዝገባቸውን/ የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  5. በጨረታው ላይ ያወጣናቸውን እቃዎች በሙሉ አሪጅናል እና ጥራቱን የጠበቁ ሆነው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ፖስታ በሚያስገቡበት ጊዜ ለተወዳደሩበት እቃ ሳምፕል የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎችን በራሳቸው ትራንስፖርት መ/ቤቱ ድረስ ማምጣት የሚችሉ፤
  8. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ ብቻ የሚወዳደሩበትን ዋጋ ቫት በመጨመርና በእያንዳንዱ ገጽ ፊርማና የድርጅቱ ማህተም በማኖር በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት በተጠቀሰው ቢሮ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. የጨረታው ማስከበሪያ በየአንዳንዱ ሎት 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸው እቃዎች አጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከጽ/ቤቱ ጋር የግዢ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን በ11ኛው ቀን የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ የጨረታው አከፋፈት ላይ ለመገኘት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን /በ11ኛው የስራ ቀን በ4፡30 ሰዓት በወረዳው አስተዳደር አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡ ተጫራቾች ለሳምፕል /ለናሙና/ ማቅረቢያ የሚያገለግላቸውን በተጫራቹ ድርጅት ቅጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

አድራሻ ፡- አራት ኪሎ አራዳ ከፍለ ከተማ ወረዳ 09 ፋይናንስ ጽ/ቤት ዳብር ህንጻ ፊት ለፊት ብርሃንና ሰላም አለፍ ብሎ ቡና ባንክ አጠገብ፡፡

ስልክ ቁጥር ፡- 011-8-68-47-83

 

በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender