ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል/ማህበር ለድርጅታችን የሥራ አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
Commercial Nominees Plc (ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ)
የጨረታ ማስታወቂያ
CN/NCB/16/17
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል/ማህበር ለድርጅታችን የሥራ አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውሉ
ሎት 1:- የሰራተኞች ደንብ ልብስ
ሎት 2፡-የሰዓት መቆጣጠሪያ (Attendance Machine)
ሎት 3፡- የተለያዩ የአይቲ እቃዎች (IT Equipments) (Heavy duty Photo copy Machine, ID Printer, Color Printer, Camera e.t.c) ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ኢንቨሎፕ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00-11፡00) ማግኘት ይቻላል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኢ ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ የካቲት 11 ቀን 2017 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ያሸነፈው ተጫራች የዕቃዎች ርክክብ የሚደረግበት ቦታ ገርጂ በሚገኘው የድርጅቱ የዕቃ ግምጃ ቤት ይሆናል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ዉጪ ይደረጋል፡፡
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ
ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር 011-1-569992
አዲስ አበባ
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
Commercial Nomminees PLC
