መድኃኒቶች እና ሪኤጀንቶች 2.የደንብ ልብሶች 3.የተለያዩ ህትመቶች 4.የተለያዩ የጽህፈት ዕቃዎች 5. የጽዳት ዕቃዎች 6. የእድሳት ጥገና እና ዕቃዎች 7. ቋሚ ዕቃዎች 8. የጄኔሬተር ጥገና 9. ለጄኔሬተር ጥገና የሚውሉ የመለዋወጫ ዕቃዎች 10. እድሳት እና ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡
በቂርቆስ ክፍስ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የቂርቆስ ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ
በቂ/ክ/ከ የቂርቆስ ጤና ጣቢያ ለ2017 ዓ/ም ለተቋሙ የሚያስፈልጉ፡-
1. መድኃኒቶች እና ሪኤጀንቶች 2.የደንብ ልብሶች 3.የተለያዩ ህትመቶች 4.የተለያዩ የጽህፈት ዕቃዎች 5. የጽዳት ዕቃዎች 6. የእድሳት ጥገና እና ዕቃዎች 7. ቋሚ ዕቃዎች 8. የጄኔሬተር ጥገና 9. ለጄኔሬተር ጥገና የሚውሉ የመለዋወጫ ዕቃዎች 10. እድሳት እና ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችል ማንኛውም ህጋዊ የንግድ ድርጅት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይየስራ ቀናት ውስጥ በጤና ጣቢያው ቅጥር ጊቢ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301 በስራ ሰዓት በመቅረብ እና የማይመለስ ብር 250.00 (ሁለት መቶ ሀምሳ ብር ብቻ) በመክፈል እና የጨረታውን ዝርዝር 9 የያዘ ሰነድ በመውሰድ መወዳደር የሚችል መሆኑን እየገለጽን ጨረታው በ10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ11፡30 ተዘግቶ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች ፡-
- በግብር ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ መያዣ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% (ፐርሰንት) በጤና ጣቢያው ስም በተዘጋጀ ሲፒኦ (CPO) ኮፒው ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማትን ለማወዳደር አስፈላጊውን የትብብር ደብዳቤ በሚከፈተው ፖስታ ማለትም በኮፒው ውስጥ በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው የንግድ ድርጅት የጠቅላላ ዋጋውን 10% በሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
- ኦሪጅናል ፖስታ በጨረታ ማወዳደሪያ ወቅት አይከፈትም፡፡
- ተጫራቾች በአቅራቢዎች ድረገጽ ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ዝርዝር ጤና ጣቢያው ባቀረበው የዋጋ ሰንጠረዥ ላይ በመሙላት እና እያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋናውን እና ኮፒውን በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው:: በተጨማሪም ቴክኒካል ሰነድ ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነድ በተለያየ ፖስታ ተሞልቶ በድጋሚ በአንድ ፖስታ መታሸግ አለበት፡፡
- ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ሁሉም ተጫራቾች ናሙና ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው::
- ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች ጥራታቸውንና ደረጃቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች መወዳደር የሚችለው ከንግድ ፈቃድ ጋር ተያያዥነት ባላቸው አቅርቦቶች አገልግሎቶች ላይ ብቻ ነው።
ማሳሰቢያ ፡- ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ የሚቀርቡት ዋጋዎች ተጨማሪ እሴት ታክስን ተርን ኦቨር ዜና ታክስን ያካተቱ መሆን አለባቸው።
አድራሻ ፡- ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ከገነት ሆቴል ወደ ሽመልስ ሀብቴ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በሚያስገባው መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- 0115536456/0115156192 በመደወል መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በቂርቆስ ክፍስ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የቂርቆስ ጤና ጣቢያ
