Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉለሌ ክ/ከተማ ት/ት ጽ/ቤት የጄኔራል ታደሰ ብሩ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address ምዕራፍ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አጠገብ 50 ሜትር ከፍ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112737095
  • Website
  • Deadline13 Feb 2025, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 10 የጄኔራል ታደሰ ብሩ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ 2017 ለመደበኛ በጀትና የውስጥ ገቢ በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የጽሕፈት እና የትምህርት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የሕንፃ መሳሪያ ዕቃዎች ፣ ሎት 3 ቋሚ የፈርኒቸር ዕቃዎች እና ሎት 4 ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ በሁለተኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በጉለሌ ክ/ከተማ ት/ት ጽ/ቤት የጄኔራል ታደሰ ብሩ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


 

ሁለተኛ ዙር የጨረታ ማስታወቂያ 002/2017

 

በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 10 የጄኔራል ታደሰ ብሩ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ 2017 ለመደበኛ በጀትና የውስጥ ገቢ በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የጽሕፈት እና የትምህርት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የሕንፃ መሳሪያ ዕቃዎች ፣ ሎት 3 ቋሚ የፈርኒቸር ዕቃዎች እና ሎት 4 ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ በሁለተኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ተጫራቾች ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርት ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡ ተጫራቾች ይህንኑ የሚገልፅ ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ምዕራፍ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አጠገብ 50 ሜትር ከፍ ብሎ ከሚገኘው በጉለሌ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 የጄኔራል ታደሰ ብሩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 202 የማይመለስ በየሎቱ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ በተጨማሪም ሰነድ 1 የገዙበትን ደረሰኝ ኮፒ ከሰነዱ ጋር አያይዘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ::
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ ጥራት ያለው ደረጃውን የጠበቀ ስለመሆኑ ናሙና ማቅረብ ላለባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የዕቃዎች ዝርዝር እና የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስማችሁን በመፃፍ ፊርማችሁንና አድራሻችሁን ማስፈርና እንደ ሚታይ አድርጋችሁ ማህተም በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በጉለሌ/ከ/ከተማ ወረዳ 10 የምዕራፍ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አጠገብ በሚገኘው የጄኔራል ታደሰ ብሩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 202 ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ስታስገቡ ከሙሉ ፋይል ኦሪጅናል እና ኮፒ ሰነድ ጋር እስከ 10ኛው ቀን 11:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባችኋል።
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣበት በ11ኛው ቀን በ4፡30 በጄኔራል ታደሰ ብሩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 202 ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል።
  6. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች በሰነድ የሰጡትን ዋጋ መለወጥ፣ ማሻሻል ወይም ከውድድሩ ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  7. የማወዳደሪያ ዋጋ ከቫት ጋር መሞላት አለበት፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 2,000 (ሁለት ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 2 ብር 2,000 (ሁለት ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 3 ብር 2,000 (ሁለት ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 4 ብር 16,000 (አስራ ስድሰት ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተመሰከረለት (CPO) በማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  9. ት/ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ የዕቃውን ብዛት ከውል በፊት 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
  10. አሸናፊው ድርጀት ዕቃዎቹን እስከ ጄኔራል ታደሰ ብሩ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ትራንስፖርት አጠቃሎ ማስገባት አለበት፡፡
  11. በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጃችሁ መወዳደር የምትችለት ባመረታችሁት ምርት ወይም እሴት በጨመራችሁት ብቻ ሲሆን ከዚህ ውጪ ግን እንደ ማንኛውም እጩ ተወዳዳሪ የጨረታ ሰነድ መግዛትና የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) በማስያዝ መወዳደር የምትችሉ ይሆናል።
  12. ተጫራቾች ዕቃውን እስከ 6 ወር 25 % ባስገቡበት ዋጋ መስሪያ ቤቱ ለመጨመር ቢጠይቅ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  13. ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለበት ውድቅ ይሆናል፡፡
  14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር +251112737095, +251118231128,0989066757

 

በጉለሌ ክ/ከተማ ት/ት ጽ/ቤት የጄኔራል ታደሰ ብሩ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

 

Save Tender