Tender Detail

Tender Details

  • Company መቱ ካርል ኮምኘሬንሲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
  • Address ኢትዮጵያ, Phone: 0917344232
  • Website
  • Deadline14 Feb 2025, 12:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Pharmaceutical Products

የመቱ ካርል ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆ/ል የህክምና መገልገያዎች፣ መድሐኒቶች፣ የላቦራቶሪ ኬሚካሎችንና የባለሞያዎች ደንብ ልብሶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

መቱ ካርል ኮምኘሬንሲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል


 

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የመቱ ካርል ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆ/ል የህክምና መገልገያዎች፣ መድሐኒቶች፣ የላቦራቶሪ ኬሚካሎችንና የባለሞያዎች ደንብ ልብሶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ነጋዴዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

  1. ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
  2. ቫት /ቲእቲ ተመዝጋቢ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
  3. በገንዘብ ጽ/ቤት በኩል በአቅራቢነት መመዝገቡን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
  4. ተጫራቾች ያሸነፉበትን የህክምና መሳሪያዎች መድሐኒቶችንና የላቦራቶሪ ኬሚካሎችን በራሳቸው ወጪ ሆስፒታሉ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. ተጫራቾች የባለሙያ የደንብ ልብሶችን እስከ ሆስፒታሉ ድረስ በመምጣት ሰራተኛውን ለክተው በትክከለኛ ልኬት ሰፍተው ሆስፒታሉ ድረስ ጨረታውን ባሸነፈው ድርጅት ወጪ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ አሽጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በሆስፒታሉ ፋይናንስ ክፍል 300 /ሶስት መቶ/ የማይመለስ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  8. የጨረታ ተሳታፊዎች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ቴክኒካሉንና ፋይናሻሉን ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም አድርጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. የጤና ባለሙያ የደንብ ልብስ ጨረታ በ11ኛው ቀን በ6፡00 ሰዓት ይዘጋና በእለቱ በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 11ኛው ቀን መደበኛ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ሆስፒታሉ ጨረታውን ከፍቶ ያወዳድራል፡፡
  10. የህክምና መሳሪያዎችን፣ መድሐኒቶችንና የላቦራቶሪ ኬሚካሎችን ጨረታው በወጣ በ12ኛው ቀን በ6፡00 ሰዓት ይዘጋና በእለቱ በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 11ኛው ቀን እና 12ኛው ቀን መደበኛ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥሉት የስራ ቀናት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ሆስፒታሉ ጨረታውን ያወዳድራል፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000 /ሠላሳ ሺህ /በባንክ የተረጋገጠ ሲፒአ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ 0917344232 / 0911020292 ይደውሉ፡፡

 

መቱ ካርል ኮምኘሬንሲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

 

Save Tender