Tender Detail

Tender Details

  • Company የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
  • Address ሸዋሮቢት ከተማ : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 033 664 0371
  • Website
  • Deadline25 Feb 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Road And Bridge Construction

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በአለም ባንክ በጀት ከዚህ በታች የተገለፀውን የከተማ ኮሪደር ልማት የግንባታ ስራ ግዢ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት


 

በድጋሚ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በአለም ባንክ በጀት ከዚህ በታች የተገለፀውን የከተማ ኮሪደር ልማት የግንባታ ስራ ግዢ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት ፤

  1. ለግንባታ ስራ የግንባታ ደረጃቸው ከደረጃ 1-6 /ከአንድ እስከ ስድስት/ ያላቸው ተቋራጮች የሆኑ ሲሆን የመልካም ስራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችልና አግባብነት ካለው የመንግስት ተቋም የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. የዘመኑን ፈቃዳቸውን ያሳደሱና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No.) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ከ 50,000 በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆን 1 አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች በሁለት ፎቶ ኮፒ አዘጋጅተው ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎችና የስራ መሳሪያዎች እና ሌሎች ሃብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መስራትና ማጠናቀቅ አለባቸው፡፡
  7. የስራ አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይቻላል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 በመክፈል ከግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 24 መውሰድ ይቻላል፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ጨረታ 130,000 /አንድ መቶ ሰላሳ ሺ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  10. የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ አንድ ዋና እና ሁለት ኮፒ ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በማሸግ በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ላይ በሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይበተጠቀሰው ቀንና ሰአት ማለትም ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን 4፡00 ሰአት ተዘግቶ 4፡30 ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
  12. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ላይ ካልሆነ ማለትም ቅዳሜና እሁድ እና በዓላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታና ሰአት ይሆናል፡፡
  13. ውድድሩ በጥቅል ወይም በሎት ስለሆነ በከፊል መሙላት አይቻልም፡፡
  14. አሰሪ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካለ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡

 

ለበለጠ መረጃ ስልክ ፡-0336640371

 

 

የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

 

Save Tender