የደ/ኢት/ክ/መ/ው/ማ/ኢነ/ቢሮ /ግ/ን/አስ/ዳይረክቶሬት ለ2017 በጀት ዓመት ሥራ አገልግሎት የሚውሉ፤ የተለያዩ ዕቃዎች፣ በግልጽ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
South Ethiopia Regional State Water, Mines And Energy Bureau (በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ ማዕድን ኢነርጂ ቢሮ)
ለዕቃ ግዥ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ኢት/ክ/መ/ው/ማ/ኢነ/ቢሮ /ግ/ን/አስ/ዳይረክቶሬት ለ2017 በጀት ዓመት ሥራ አገልግሎት የሚውሉ፤
- ሎት -1 የተለያዩ አላቂ ዕቃዎች፣
- ሎት -2 የተለያዩ ሌሎች አላቂ ዕቃዎች፣
- ሎት -3 የተለያዩ የመኪና ዕቃዎች፣
- ሎት -4 የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
በዘርፋቸው ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ካላቸው በግልጽ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ማንኛውም በነዚሁ ንግድ ዘርፍ ላይ የተሠማሩ ህጋዊ ነጋዴዎች በውድድሩ ላይ እንዲካፈሉ እየጋበዝን በውድድሩ ላይ ለመካፈል ቀጥሎ የቀረቡትን መመዘኛዎች ወይም መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የአቅርቦት ምዝገባ የምስክር ወረቀትና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለመወዳደር ሲፈልጉ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከደ/ኢ/ው/ማዕ/ኢነርጂ ቢሮ ሁለተኛ ፎቅ /ግ/ን/አስ/ዳይረክቶሬት በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ በመሙላት ለሎት 1፣ 2 እና 3 አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ ለየብቻ እንዲሁም ለሎት 4 ለቴክኒካልና ፋይናንሽያል አንዳንድ ኦሪጅናልና ለእያንዳንዳቸው ሁለት ኮፒ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ይዘው በመቅረብ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ያለባቸው ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በ16ኛው ቀን ልክ በ3:00 ሰዓት ይከፈታል:: ነገር ግን ይህ ቀን በዓል ወይም ሰንበት ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ እስከ መ/ቤቱ ቅጥር ግቢ ዲላ አጓጉዘው ማስረከብ አለባቸው፡፡
- ከወጣው ጨረታ ውስጥ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ዋጋ ባለው ግዥ የሚሳተፉ ማንኛውም የአገር ውስጥ ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃ ያቀረቡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 የሥራ ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ ማብራሪያ የደ/ኢ/ክ/መ/ው/ማ/ኢነ/ቢሮ ግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት በስልክ ቁጥር 09 92 66 98 98 ወይም 09 12 04 34 23 መጠየቅ ይቻላል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ውሃ ማዕድን ኢነርጂ ቢሮ
