የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2017 የበጀት ዓመት የተለያዩ የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦች ለሁለተኛ ጊዜ ፤ እንጀራ ለሁለተኛ ጊዜ እና ለኮሚኒቲ ፊርማሲ መድኃኒቶች ለአንደኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Adama Hospital Medical College (የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2017 የበጀት ዓመት
- የተለያዩ የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦች ለሁለተኛ ጊዜ እና
- እንጀራ ለሁለተኛ ጊዜ
- ለኮሚኒቲ ፊርማሲ መድኃኒቶች ለአንደኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላላችሁ።
- የ2017 ዓ.ም የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ በዘርፉ ያላችሁ፡፡
- ተጫራቾች የተጨመሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆን መረጃ ማቅረብ የሚችል። በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባችሁን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ ግዥ መ/ቤት ድረስ በራሱ ወጪ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ኮፒና ኦሪጅናል ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማሸግ አለባቸው።
- ስርዝ ድልዝ ያለው፤ የማይታይ የጨረታ ሰነድ ወይም የዋጋ ዝርዝር ተቀባይነት የለውም።
- ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% ማስያዝ የሚችል፡፡
- ይህ ማስታወቂያ ከጣበት ቀን ጀምሮ ከኮሌጁ ግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ክፍል ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ የተለያዩ የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦች እና ለእንጀራ 100/መቶ ብር/፣ በኮሚኒቲ ፋርማሲ መድኃኒቶች 200/ ሁለት መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ አለባቸው፡፡
- የተለያዩ የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦች ጨረታው የሚከፈተው በ12/6/2017ዓ.ም 8፡30 ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- እንጀራ ጨረታው የሚከፈተው በ12/6/2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡30 ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የኮሚኒት ፋርማሲ መድኃኒቶች ጨረታው የሚከፈተው በ13/6/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉትን ዋጋ በመሥሪያ ቤቱ ሰነድ ብቻ ላይ መሆን አለበት፡፡
- ጨረታው ማስከበሪያ ለተለያዩ የምግብ ሸቀጣሸቀጦች እና ለእንጀራ ለእያንዳንዱ ለየብቻ 10,000 (አሥር ሺ) ብር ለኮሙኒቲ ፋርማሲ መድኃኒቶች 20,000 (ሃያ ሺህ) ብር በ “CBE, CBO, እና በSiqe'' በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 022 812 3956 ደውለው መረዳት ይችላሉ፡፡
አዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ
