በአብክመ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በ2017 በጀት አመት የእግረኛ መንገድ (Walk Way) ለማሰራት በጠቅላላ ስራ ተቋራጭ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
የእግረኛ መንገድ (Walk Way) ስራ ብሄራዊ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በ2017 በጀት አመት የእግረኛ መንገድ (Walk Way) ለማሰራት በጠቅላላ ስራ ተቋራጭ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በሥራው ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆኑ፡-
- በጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ደረጃቸው GC/7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፤
- ስራው በጠቅላላ ስራ ተቋራጭ አግባብነት ያለው ህጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና ያሳደሱ፤ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና TIN ያላቸው፡፡
- የጨረታውን ሰነድ ከከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረት ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 33 በግዢ/ፋይ/ ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናና ኮፒ በመያዝ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን የፋይናንሽያል ሰነድ ዋና እና ኮፒ በማድረግ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብክመ ከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሃያ ሁለተኛው ቀን (22ኛ ቀን) 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ17/5/2017 ዓ.ም በ22ኛው 4፡30 ሰዓት በግዢ /ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 22ኛው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 225,000 (ሁለት መቶ ሃያ አምስት ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይንም በተረጋገጠ በባንክ ትዕዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚዋዋልበት ጊዜ የውለታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ድምር ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለፋይናንስ ግምገማ ያለፉት ተጫራቾች በቁጥር ቢያንስ 3 እና በላይ ከሆኑ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት (አርቲሜቲክ ቼክ) ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ 2.5% ድረስ ከሆነ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ የበለጠ ልዩነት ካጋጠመ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- ከ3 በታች ከሆኑ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት (አርቲሜቲክ ቺክ) ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ 1% ድረስ ብቻ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ በላይ ከሆነ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- የሂሳብ ስሌት (አርቲሜቲክ ቼክ) በግዥ ፈፃሚው መ/ቤት ባለሙያ ከሚስተካከለው ውጭ በተጫራቾች የሚቀርበው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር 033 554 02-55 ደውለው መረዳት ይችላሉ፡፡
በአብክመ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
