የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ለ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ/አ/ከ/አ/የሰ/ፀ/አስ/ቢሮ ዕቃ/አገ/ግ/ጨ/005/2017ዓ/ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ለ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች
ሎት 2 የመኪና ዕቃዎች
ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ
ሎት 4. የሻይ ቡና ዕቃዎች
ሎት 5 የመድረክ አስተዋዋቂ
ሎት 6 ህትመት
ሎት 7 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና አገልግሎት
ሎት 8 የደንብ ልብስ/አንጸባራቂ
ስለሆነም ጨረታውን መካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያዎች በማሟላት መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ቲን እና /VAT/ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር / በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ፒያሳ ከሚገኘው ከንቲባ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ከመ/ቤቱ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሚወዳደሩበት ሎት በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም የባንክ ዋስትና /unconditional/ በመ/ቤታችን ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የኢንሹራንስ ዋስትና አንቀበልም።
- ሎት1. የጽህፈት መሳሪያ———3,000.00 (ሶስት ሺህ ብር)
- ሎት2 የመኪና ዕቃዎች———5,000.00 (ስምስት ሺህ ብር)
- ሎት3 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ————5,000.00(አምስት ሺ ብር)
- ሎት 4 የሻይ ቡና ዕቃዎች———1,000.00(አንድ ሺህ ብር)
- ሎት5 የመድረክ አስተዋዋቂ——— 3,000.00 (ሶስት ሺህ ብር)
- ሎት6 ህትመት———2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)
- ሎት7. የኤሌክትሮኒክስ ጥገና አገልግሎት——— 5,000.00(አምስት ሺህ ብር)
- ሎት 8. የደንብ ልብስ/አንጸባራቂ———10,000.00 (አስር ሺህ ብር)
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ሞልተው በመፈረም እና ህጋዊ ማህተም በማድረግ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ኦሪጅናል እና ኮፒ በየሎቱ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተራ ቁጥር 2 በተጠቀሰው አድራሻ የመ/ቤቱ ግዢ ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 11ኛው ቀን እስከ 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በመ/ቤቱ ዋጋ መሙያ ያልተሞላ ዋጋ ፊርማና ማህተም የሌለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡30 ላይ ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል። ናሙና የተጠየቀባቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት እያንዳንዱ ዕቃ ጥራት በቴክኒክ ብቃታቸው ከተመረጡ በዋጋ የሚወዳደሩ ይሆናል። አማራጭ ጨረታ አይፈቀድም፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ባሸነፈበት ጠቅላላ ዕቃዎች ዋጋ 10 በመቶ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ አሸናፊነቱ ከታወቀበት ከ7ኛው ቀን ጀምሮ በ 7 ቀናት ውስጥ ውል መፈረም አለበት።
- በተራ ቁጥር 7 መሰረት ውል የማይፈጽሙ አሸናፊዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ ለመንግስት ገቢ በማድረግ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ መጠቀም ይችላል።
- አሸናፊ የሆነ ድርጅት አሸናፊ የሆነባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ከንቲባ ጽ/ቤት ምድር ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ለመ/ቤቱ ማስረከብ ይኖርበታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 11 57 54 39 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ
